Loading
Singer
ጌታዬ ፡ ለዚህ ፡ ያደረስኸኝ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ? ጌታዬ ፡ ለዚህ ፡ ያበቃኸኝ ፡ እኔ ፡ ማን ፡ ነኝ? ከየት ፡ ነው ፡ የመጣሁት ፡ ያነሳኸኝ ፡ ጌታ? የበግ ፡ ኮቴ ፡ ስከተል ፡ ነበር ፡ ጥዋት ፡ ማታ ከሳኦል ፡ ከፍልስጥኤም ፡ ከአማሌቅ ፡ ሁሉ ተርፌአለሁ ፡ የአንተ ፡ ጋሻነት ፡ በመኖሩ አሁንም ፡ እባብ ፡ ጊንጡን ፡ ረግጬ ፡ እኖራለሁ በዓለም ፡ ለዘለዓለም ፡ ስምህን ፡ እባርካለሁ አንደበቴ ፡ ተከፍቶ ፡ ዛሬ ፡ እናገራለሁ ሽባነቴም ፡ ቀርቶ ፡ እንደልብ ፡ እራመዳለሁ ያሰሩኝ ፡ የገዙኝ ፡ አጋንንት ፡ ለሞቴ ጥለው ፡ ሸሹ ፡ ጌታዬ ፡ አንተን ፡ ሲያዩ ፡ በሕይወቴ ምንም ፡ የለም ፡ ከታሰርኩት ፡ ሁሉ ፡ ተፈትቻለሁ ዘመኔን ፡ አንተን ፡ ክበር ፡ እያልኩ ፡ እኖራለሁ ጠላቶቼንም ፡ ከእግሮቼ ፡ በታች ፡ አስገዝተሃል ዘንዶውን ፡ በስለታም ፡ ሰይፍህ ፡ አንተ ፡ ወግተሃል እባብ ፡ ጊንጥን ፡ ልረግጥ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ የእኔ ፡ ድርሻ ልኖር ፡ ነው ፡ በቤትህ ፡ ሳመልክህ ፡ እስከመጨረሻ ሳስበው ፡ ይህ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ደስታዬ ጥልቅ ፡ ነው ፡ የእኔን ፡ ፍቅር ፡ ለአንተ ፡ መግለጫዬ ይበቃኛል ፡ አሁንም ፡ ከአንተው ፡ ጋር ፡ እስማማለሁ አልማዝ ፡ ዕንቁ ፡ ጣኦቴን ፡ ከድንኳን ፡ አርቃለሁ የኦፊር ፡ ወርቄን ፡ በጅረት ፡ ድንጋይ ፡ ውስጥ ፡ ልጥል