Loading
Singer
ማደግ ፡ እሻለሁ ፡ አንተን ፡ መምሰል ግን ፡ አቅቶኛል ፡ ክብሬን ፡ መጣል የዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ ልቤን ፡ አድክሞት ለአንተ ፡ እንዴት ፡ ልኖር ፡ ለሌላው ፡ ሳልሞት የዚህ ፡ ዓለም ፡ ነገር ፡ ልቤን ፡ አዝሎት ለአንተ ፡ እንዴት ፡ ልኖር ፡ ለሌላው ፡ ሳልሞት አዝ፦ ለውጠኝ (፫x) ፡ ለውጠኝ (፫x) ቃል ፡ ኪዳኔን ፡ ያጠፍኩኝ ደካማ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ እንዲያው ፡ አያለሁ ፡ ልብ ፡ ብዬ እጮሃለሁ ፡ እንዲህ ፡ ብዬ (፪x) እጄን ፡ ያዘኝና ፡ አስጠጋኝ ወደራስህ ፡ ሳበኝ (፪x) ከካቻምና ፡ የአምና ፡ ከአምናው ፡ የዘንድሮ ሕይወቴ ፡ ካልታየ ፡ ስምህ ፡ በእኔ ፡ ከብሮ መኖርስ ፡ ምንድንነው ፡ ዘመን ፡ ማስቆጠሩ እንዲያው ፡ መመላለስ ፡ ፍሬን ፡ ሳያፈሩ አዝ፦ ቃል ፡ ኪዳኔን ፡ ያጠፍኩኝ ደካማ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ እንዲያው ፡ አያለሁ ፡ ልብ ፡ ብዬ እጮሃለሁ ፡ እንዲህ ፡ ብዬ (፪x) እጄን ፡ ያዘኝና ፡ አስጠጋኝ ወደራስህ ፡ ሳበኝ (፪x) የእምነት ፡ አባቶቼ ፡ አንተን ፡ አስከብረው የክብርን ፡ ሞት ፡ አዩ ፡ በእምነታቸው ፡ ጸንተው ፀጋህን ፡ አልብሰኝ ፡ አልኑር ፡ ተሸንፌ ከሚጠፋው ፡ ዓለም ፡ ጸጸትን ፡ አትርፌ አዝ፦ ቃል ፡ ኪዳኔን ፡ ያጠፍኩኝ ደካማ ፡ ሰው ፡ እኔ ፡ ነኝ እንዲያው ፡ አያለሁ ፡ ልብ ፡ ብዬ እጮሃለሁ ፡ እንዲህ ፡ ብዬ (፪x) እጄን ፡ ያዘኝና ፡ አስጠጋኝ ወደራስህ ፡ ሳበኝ (፪x)