Loading
Singer
ላንተ ክብርን ሳቀርብ - ስሰዋ ምስጋና በልኬ ሰፍቼ እንዳላሳንስህ - እፈራለሁና ደስ በሚያሰኝህ - አይነት እንዳመልክህ አንተን አስተምረኝ - እንዳውቅህ በልክህ ልወቅህ ጌታዬ - ደስ ተሰኝብኝ በቃየን መሰዊያ - መስዋዕቴ አይገኝ - [አዝ] ነፍሴ ሀሴት አድርጋ - ዝማሬ ‘ሰማለሁ ከሚያመልኩህ ጋራ - አብሬ አምልኬአለሁ “አባት አልልህም” - ሲሉህ አጅቤኣለሁ ግን ካንተ ወዲያ አባት - ከየት አገኛለሁ? [አዝ] ልወቅህ ጌታዬ - ልሁን ባንተ ቅጥር ባንተ ድልን ሳገኝ - ጦሬን እንዳልቆጥር - 2x ላንተ የማቀርበው - ንጹህ መስዋዕቴ ምሉዕ እንዲሆንልኝ - ቢሳካ ምኞቴ ልቦናዬን አብራው - ክብርህን እንዳየው ከስጦታ በላይ - ሰጪውን ልለየው! [አዝ] ትወቅህ ይኽች ልቤ - በቃልህ አሙቃት እንዳሻት እንዳትሆን - ከጥፋት ጠብቃት - 2x ሁሌ እንደለመድኩት - ስላደረግከው ድንቅ ወይም ድል ለማግኘት - ስለከበበኝ ጭንቅ አይሁን ጌታዬ ሆይ - ስብከቴን ጨምቄ ላምልክ እንጂ ገብቶኝ - ክብርህን አውቄ