Loading
Singer
Updated 3d ago
ልዑልን ፡ መጠጊያ ፣ መጠጊያ ያደረገው ፡ ሰዉ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል የለም ፡ የሚያሰጋዉ (፪x) ጌትዬን ፡ መጠጊያ ፣ መጠጊያ ያደረገው ፡ ሰዉ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል የለም ፡ የሚያሰጋዉ (፪x) ተስፋን ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነው (፫x) እንደተናገርው ፡ እንዲሁ ፡ አረገው እንዲሁ ፡ አረገው ፣ እንዲሁ ፡ አረገው (፪x) እንደተናገርው ፡ እንዲሁ ፡ አረገው ፣ እንዲሁ ፡ አረገው (፪x) እንደተናገርው ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው ፣ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (፪x) አይመስለኝም ፡ ነበር ፡ ጌታ ፡ ያለው ፡ የሚፈጸም ኑሮዬን ፡ ሕይወቴን ፡ ዞር ፡ ብዬ ፡ ሳየው ይህ ፡ ሁሉ ፡ ይሁን ፡ እንጂ ፡ ያለው ፡ ግን ፡ ይሆናል እርሱ ፡ መች ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ ተናግሮ ፡ ዝም ፡ ይላል ያለው ፡ ይፈፀማል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ያለው ፡ ይፈፀማል (፪x) ለእርሱ ፡ ምን ፡ ይሳናል (፪x) ልዑልን/ጌትዬን ፡ መጠጊያ ፣ መጠጊያ ያደረገው ፡ ሰዉ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል የለም ፡ የሚያሰጋዉ (፪x) ተናግሮ ፡ ማድረግን ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያውቃል ታዲያ ፡ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ብሎሃል ጠብቀው ፡ ተስፋህን ፡ አትወላውል ፡ ጽና የተናገረህን ፡ ሲፈፅም ፡ እንድታይ ያለው ፡ ይፈፀማል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ያለው ፡ ይፈፀማል (፪x) ለእርሱ ፡ ምን ፡ ይሳናል (፪x) ተስፋን ፡ የሰጠው ፡ የታመነ ፡ ነው (፫x) እንደተናገርው ፡ እንዲሁ ፡ አረገው (፫x) እንደተናገርው ፡ እንዲሁ ፡ አረገው ፣ እንዲሁ ፡ አረገው (፪x) እንደተናገርው ፡ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው ፣ ነው ፡ ለእኔ ፡ ያረገው (፪x) ተናግሮ ፡ ማድረግን ፡ እርሱ ፡ ብቻ ፡ ያውቃል ታዲያ ፡ እህቴ ፡ ሆይ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ብሎሻል ጠብቂው ፡ ተስፋህን ፡ አትወላውይ ፡ ጽኚ የተናገረሽን ፡ ሲፈፅም ፡ እንድታዪ ያለው ፡ ይፈፀማል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው ያለው ፡ ይፈፀማል (፪x) ለእርሱ ፡ ምን ፡ ይሳናል (፪x) ልዑልን/ጌትዬን ፡ መጠጊያ ፣ መጠጊያ ያደረገው ፡ ሰዉ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል የለም ፡ የሚያሰጋዉ (፪x)