Loading
Singer
አዝ፦ ልዑል ፡ መጠጊያህ ፡ ሰፊ ፡ ነው ልዑል ፡ መደሪያህ ፡ ምቹ ፡ ነው ልዑል ፡ ማረፊያህ ፡ ሰላም ፡ ነው ያለሥጋት ፡ እኖራለሁ (፪x) ሊያስፈራሩኝ ፡ የሞከሩ ፡ ሊያጐሳቁሉኝ ፡ የጣሩ አሏዋለላቸውም ፡ በቃ ፡ ልዑል ፡ አምላክ ፡ አለኝ ፡ ለካ ስለገባሁ ፡ በመዳፉ ፡ ጠላቶቼ ፡ እንዲያው ፡ ለፉ በእኔና ፡ በእነርሱ ፡ መኻል ፡ ብርቱ ፡ ቅጥር ፡ ጌታ ፡ ሰርቷል (፪x) ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ በ???? ፡ ባዮች ፡ ተሸፍኜ ፡ በክንፎችህም ፡ ተማምኜ እውነት ፡ እንደ ፡ ጋሻ ፡ ከቦኝ ፡ ከአደጋ ፡ ሁሉ ፡ አስጥሎኝ ሳልደነግጥም ፡ ሳልፈራ ፡ ኢኸው ፡ ስኖር ፡ ከአንተ ፡ ጋራ መኖሪያህ ፡ ተመችቶኛል ፡ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያሻኛል (፪x) አዝ፦ ልዑል ፡ መጠጊያህ ፡ ሰፊ ፡ ነው ልዑል ፡ መደሪያህ ፡ ምቹ ፡ ነው ልዑል ፡ ማረፊያህ ፡ ሰላም ፡ ነው ያለሥጋት ፡ እኖራለሁ (፪x) አንተ ፡ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ መሸህሰጊያዬ ፡ ነው ፡ ስምህ ክፉ ፡ ነገር ፡ አይቀርበኝም ፡ መቅሰፍትም ፡ አያገኘኝም በመንገዴ ፡ እንዲጠብቁኝ ፡ መላእክትህን ፡ ታዛለህ እግሬም ፡ እንዳይሰናከል ፡ በእጆችህ ፡ ታነሳኛለህ (፪x) ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ ሃ ፡ ሃሌሉያ (፫x) ፡ ሃሌሉያ