Loading
Singer
አልሰለችም ፡ ፍፁም ፡ ደግሞም ፡ አልታክትም ምሥጋናን ፡ ከማለት ፡ ከቶ ፡ ዝም ፡ አልልም ምሕረትህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ በዝቶልኝ ፡ ስላየሁ ተመስገን ፡ እያልኩኝ ፡ ለአንተ ፡ እዘምራለሁ አዝ፦ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x) ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x) ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው ከአዕምሮዬ ፡ በላይ ፡ አድርገህልኛል እጅህን ፡ ዘርግተህ ፡ ጌታ ፡ ባርከኸኛል ለዚህ ፡ የምሰጥህ ፡ ምላሽ ፡ ስለሌለኝ ምሥጋናን ፡ እሰዋለሁ ፡ ለአንተ ፡ ለወደድኸኝ አዝ፦ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x) ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x) ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው ታላቁን ፡ ሥራህን ፡ ማዳንህን ፡ ያዩ ዘወትር ፡ ሳይታክቱ ፡ ለአንተ ፡ ይቀኛሉ እኔም ፡ የእጅህን ፡ ሥራ ፡ በዓይኔ ፡ ስላየሁ ጠዋትና ፡ ማታ ፡ ለክብርህ ፡ እቀኛለሁ አዝ፦ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x) ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x) ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው ምሥጋናን ፡ የሚሠዋ ፡ እርሱ ፡ ያከብረኛል በማለት ፡ በቃልህ ፡ ጌታ ፡ ተናግረሃል እኔም ፡ አንተን ፡ ሳከብር ፡ (እጅግ) ደስ ፡ ይለኛል ይኸው ፡ ፊትህ ፡ ቆምኩኝ ፡ ልሠዋ ፡ ምሥጋና ምሥጋና ፣ ምሥጋና (፭x) ይገባዋልና ዘንድሮ ፡ ምሥጋና ፡ በዛ ፡ በዛ ፡ አሉ መዝነው ፡ ለክተው ፡ መስጠት ፡ የለመዱ ግን ፡ ሊበዛ ፡ ቀርቶ ፡ እንደውም ፡ አንሶታል በእውነትና ፡ መንፈስ ፡ መቼ ፡ ሰጥተውታል እኔ ፡ ግን ፡ ስሰዋ ፡ ምሥጋናን ፡ ለአምላኬ ሳልመዝን ፡ ሳልሰፍር ፡ ሰጠሁ ፡ ተንበርክኬ በእውነትና ፡ መንፈስ ፡ ሳመልከው ፡ አይደክመኝም ምሥጋናን ፡ ስሰዋ ፡ አይታወቀኝም ምሥጋና ፣ ምሥጋና (፭x) ይገባዋልና በጌታዬ ፡ ካመንኩኝ ፡ ጊዜ ፡ ጀምሮ ምህረት ፡ ቸርነቱ ፡ አያልቅም ፡ ተነግሮ ታዲያስ ፡ ካላስቆመ ፡ የእርሱ ፡ በጐነት ምሥጋናን ፡ እንዴት ፡ ላቁም ፡ በእርሱ ፡ አለኝ ፡ ቸርነት ብር ፡ ወርቅ ፡ ወይም ፡ አልማዝ ፡ ገንዘብ ፡ ወይም ፡ ዕንቁ ያረገውን ፡ ውለታ ፡ ስራ ፡ ብቂ ከምሥጋና ፡ ሌላ ፡ ክፍያ ፡ አይፈልግም እርሱን ፡ ከማመስገን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ አልልም ምሥጋና ፣ ምሥጋና (፭x) ይገባዋልና ኢየሱስ ፡ ምህረቱን ፡ እያበዛላችሁ ግን ፡ ምሥጋናን ፡ መስጠት ፡ የደካከማችሁ ያከብረኛል ፡ ካለ ፡ ምሥጋናን ፡ የሚሰው የምን ፡ ቁጠባ ፡ ነው ፡ ላታገኘው ፡ ዋጋ እኔስ ፡ ተነሳብኝ ፡ ምሥጋናን ፡ ተሞላሁ ቁጠባን ፡ አላቅም ፡ ስለት ፡ ካላስገባሁ ያውም ፡ ነፍሱን ፡ ሰጥቶኝ ፡ አነሳ ፡ ምሥጋና ሳመልክ ፡ ላሳያችሁ ፡ ክብሬን ፡ ልጣልና ምሥጋና ፣ ምሥጋና (፭x) ይገባዋልና አዝ፦ ልዑል ፡ ሆይ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x) ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ለሥምህ ፡ ክብር ፡ ዘምራለሁ (፪x) ምሥጋናህም ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x)