Loading
Singer
አዝ፦ አቤኔዘር ፡ አቤኔዘር ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን አቤኔዘር ፡ አቤኔዘር ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን እስካሁን ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን እስካሁን ፡ እግዚአብሔር ፡ እረዳን (፪x) እኛም ፡ ደግሞ ፡ የረዳንን ልዑል ፡ እግዚአብሔርን ፡ እናመልካለን . (1) . ፡ ኮረብቶች ፡ ወንዞችን ፡ አፈሰሱ በሸለቆችም ፡ መካከል ፡ ምንጮች ፡ ተከፈቱ ምድረበዳው ፡ ረሰረሰ ፡ ከጥማት ፡ ምድር ፡ ውኃ ፡ ፈለቀ እግዚአብሔር ፡ አምላክ ፡ የእኛን ፡ ጩኸት ፡ አደመጠ በእኛ ፡ ላይ ፡ ታወቀ አዝ፦ አቤኔዘር ፡ አቤኔዘር ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን አቤኔዘር ፡ አቤኔዘር ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን ብቻውን ፡ እግዚአብሔር ፡ ረዳን ብቻውን ፡ እግዚአብሔር ፡ እረዳን (፪x) እኛም ፡ ደግሞ ፡ የረዳንን ልዑል ፡ እግዚአብሔርን ፡ እናመልካለን ወጥመድ ፡ ቢዘረጋ ፡ አሃሃሃሃ ፡ ጉድጓድም ፡ ቢቆፍር ጠላቴ ፡ ሊይዘኝ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ቢሞክር ቢመስለኝም ፡ ምወድቅ ፡ ፈጽሞ ፡ ምጠፋ ጌታዬ ፡ ሆኖኛል ፡ የዘለዓለም ፡ ተስፋ ፡ አሜን ስለዚህ ፡ አለሁ ፡ አልጠፋሁም ሸንበቆን ፡ አልተደገፍኩም ይረዳኛል ፡ ኃይሌ ፡ ነው በአምላኬ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ (፪x) አምላክ ፡ ነህና ፡ አምላክ ፡ ነህና (፪x) ላምልክህ ፡ እንደገና (፬x) አምላክ ፡ ነህና ፡ ላምልክህ ፡ እንደገና አምላክ ፡ ነህና ፡ ላምልክህ ፡ እንደገና አንዳንዶች ፡ የሰይጣን ፡ ቀንበሩ ፡ ከብዷቸው ጅማሬ ፡ ላይ ፡ ቀሩ ፡ ጠፍቶ ፡ ሚረዳቸው ሲያገለግሉ ፡ ሰይጣንን ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ሲሉ ተሰብሮ ፡ ወጋቸው ፡ ምርኩዙ ፡ ጠፍተው ፡ በዚያው ፡ ቀሩ እኔ ፡ ግን ፡ አለሁ ፡ አልጠፋሁም ቀንበር ፡ ከብዶኝ ፡ አልጐበጥኩም ቀና ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ በአምላኬ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ በፀጋሁ ፡ አለሁ ፡ አልጠፋሁም ቀንበር ፡ ከብዶኝ ፡ አልጐበጥኩም ቀና ፡ ብዬ ፡ እሄዳለሁ በአምላኬ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ ከአንተ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ ማነው? ሌላ ፡ አምላክ ፡ ማነው? (፪x) ሳስብህ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ኩራትም ፡ ይሰማኛል ከልቤ ፡ ደስታ ፡ ፈንቅሎ አዘለለኝ ፡ ወጣሁ ፡ ከእሮሮ (፭x)