Loading
Singer
ለሰው ፡ አላወራም ፡ ምን ፡ ትርፍ ፡ አገኛለሁ ሃዘኔን ፡ ብሶቴን ፡ ላንተው ፡ እነግራለሁ ደጃፌን ፡ ዘግቼ ፡ አጫውትሃለሁ አምናለሁ ፡ ካንተ ፡ ዘንድ ፡ ምላሽ ፡ አገኛለሁ (፪x) አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ፡ ላንተው ፡ እነግራለሁ ትካዜዬን ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አረግሃለሁ (፪x) የኤርትራን ፡ ባህር ፡ ታሻግረኛለህ ከሰማያት ፡ መናን ፡ ታወርድልኛለህ ሃሳብህም ፡ ከቶ ፡ አይከለከልም ሁሉ ፡ ይቻልሃል ፡ ምንም ፡ አይከብድህም (፪x) አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ፡ ላንተው ፡ እነግራለሁ ትካዜዬን ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አረግሃለሁ (፪x) የነገሩህንም ፡ የማትረሳ ፡ ነህ አንዱም ፡ አይጠፋህም ፡ ታስታውሰዋለህ ሕመሜን ፡ በሙሉ ፡ አንተ ፡ ታውቀዋለህ መድኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ትፈውሰኛለህ (፪x) አዝ፦ የሚያስጨንቀኝን ፡ ላንተው ፡ እነግራለሁ ትካዜዬን ፡ ሁሉ ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እጥላለሁ የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አረግሃለሁ (፪x) ::የመድኃኒቴ ፡ አምላክ ፡ ተስፋ ፡ አረግሃለሁ (፫x)