Loading
Singer
መዋረዳቸውን ፡ አይተህ ፡ አንተ ፡ ባርከሃቸው የቤትህን ፡ ልጆች ፡ አንተ ፡ ሰብረሃቸው ትዕቢታቸው ፡ ቀርቶ ፡ በትሁት ፡ ልባቸው እንባቸውን ፡ ሲያፈሱት ፡ ለአንተ ፡ አየኋቸው አዝ፦ ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ ፡ ልቤን ፡ ስበርልኝ እኔነቴ ፡ ቅርቶ ፡ ጸጋህ ፡ እንዲበዛልኝ ትዕቢቴን ፡ ሽረህ ፡ ትህትና ፡ አልብሰኝ (፪x) ጌታ ፡ ዘወትር ፡ መሰበርን ፡ ሽቼ አብዝቼ ፡ እጮሃለሁ ፡ ሌተቀን ፡ ተግቼ እስከመቸ ፡ ድረስ ፡ ሕይወቴ ፡ እንዲህ ፡ ደርቆ እኖራለሁ ፡ ጌታ ፡ ልምላሜ ፡ አርጐ አዝ፦ ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ ፡ ልቤን ፡ ስበርልኝ እኔነቴ ፡ ቅርቶ ፡ ጸጋህ ፡ እንዲበዛልኝ ትዕቢቴን ፡ ሽረህ ፡ ትህትና ፡ አልብሰኝ (፪x) የመሰበር ፡ ፍላጐቴ ፡ ግለቱ ፡ ሳይበርድ ሰማዬችን ፡ ከፍተህ ፡ ምነው ፡ ብትወርድ ምርኩዜን ፡ ፈትነህ ፡ እባክህ ፡ ስበረኝ ትሁትና ፡ ታዛዥ ፡ መሆን ፡ አስተምረኝ አዝ፦ ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ ፡ ልቤን ፡ ስበርልኝ እኔነቴ ፡ ቅርቶ ፡ ጸጋህ ፡ እንዲበዛልኝ ትዕቢቴን ፡ ሽረህ ፡ ትህትና ፡ አልብሰኝ (፪x) የራሴን ፡ ማንነት ፡ ያኔ ፡ በርግጥ ፡ እረዳለሁ የውስጥ ፡ ዓይኔ ፡ በርቶ ፡ አብዝቼም ፡ አያለሁ በፍፁም ፡ ግልጽነት ፡ ስምህን ፡ አውጃለሁ በበረከት ፡ ሙላት ፡ አስከብርሃለሁ አዝ፦ ለእኔም ፡ አባቴ ፡ ሆይ ፡ ልቤን ፡ ስበርልኝ እኔነቴ ፡ ቅርቶ ፡ ጸጋህ ፡ እንዲበዛልኝ ትዕቢቴን ፡ ሽረህ ፡ ትህትና ፡ አልብሰኝ (፪x)