Loading
Singer
አሻግሬ ፡ አያለሁ ፡ ያንተን ፡ መልካምነት ከቶ ፡ አልገምትህም ፡ አሁን ፡ ባለሁበት ታሪክ ፡ የምትለውጥ ፡ ሁሉንም ፡ የምትቀይር እኔ ፡ የማመልክህ ፡ ድንቅነህ ፡ እግዚአብሔር አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ በጐና ፡ ያማረ ፡ ነው (፫x) አመሰግንሃለሁ (፫x) አመሰግንሃለሁ (፫x) የተገለጠውን ፡ ነገር ፡ ጸራለህ በላይ ፡ ተሰውረህ ፡ ድንቅን ፡ ታደርጋለህ ተዐምራትህ ፡ ብዙ ፡ እጅግ ፡ የበዛ ፡ ነው ጌታ ፡ አሰራርህ ፡ ከሁሉም ፡ ልዩ ፡ ነው አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ በጐና ፡ ያማረ ፡ ነው (፫x) አመሰግንሃለሁ (፫x) አመሰግንሃለሁ (፫x) ከሁኔታዎች ፡ በላይ ፡ ቃልህን ፡ አምናለሁ ሚሰማኝን ፡ ሳይሆን ፡ የሩቁን ፡ አያለሁ ከእንግዲህ ፡ ታምኜ ፡ በእምነት ፡ እኖራለሁ የተናገርከኝንም ፡ እንዳገኝ ፡ አውቃለሁ (፪x) ኃይልህ ፡ ብዙ ፡ ሳለ ፡ ጠላቶች ፡ ቢዋሹም አንተ ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ከቶ ፡ አትለወጥም መልካምነትን ፡ በማድረግ ፡ ደስ ፡ ይለሃልና አቤቱ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ይሁን ፡ ለአንተ ፡ ምሥጋና አዝ፦ ለእኔ ፡ የምታስበው ፡ በጐና ፡ ያማረ ፡ ነው (፫x) አመሰግንሃለሁ (፫x) አመሰግንሃለሁ (፫x)