Loading
Singer
አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው መስቀል ፡ ተሸክመህ ፡ ደፋ ፡ ቀና ፡ ብለህ በፈጠርከው ፡ ፍጥረት ፡ እየተንገላታህ እጅጉን ፡ ተንቀህ ፡ በጣምም ፡ ተዋርደህ እኔን ፡ አድነሃል ፡ ይግነን ፡ ታላቅ ፡ ስምህ (፪x) አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው ለአይምሮ ፡ በሚክብድ ፡ በዘግናኝ ፡ ሁኔታ እጅህና ፡ እግርህ ፡ በሚስማር ፡ ተመታ ያለ ፡ እንዳች ፡ ርህራሄ ፡ ኢየሱስ ፡ በጭካኔ ግፍ ፡ አደረሱብህ ፡ ተሰቃየህ ፡ ለእኔ (፪x) አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው ከወንበዴዎች ፡ ጋር ፡ ሰቀሉህ ፡ ኢየሱስ ከላይ ፡ የወረድህ ፡ ሳለህ ፡ የዓለም ፡ ንጉስ ሆምጣጤም ፡ አጠጡህ ፡ ጨከኙ ፡ በብዙ ጌትነትህ ፡ የታል ፡ እያሉ ፡ እያፌዙ (፪x) አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው በእንጨት ፡ ተሰቅለህ ፡ እንደ ፡ መርገም ፡ ሰው ለጠላቶችህ ፡ ማለድኽ ፡ ፍቅርህ ፡ ሰፊ ፡ ነው ተፈጸመም ፡ አልህ ፡ ነፍስህን ፡ ሰጠህ ፡ ለኔ ከፍ ፡ በል ፡ ተባረክ ፡ ዘላለም ፡ መድህኔ (፪x) አዝ፦ ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ልዩ ፡ ነው ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ልዩ ፡ ነው አይምሮን ፡ ያልፋል ፡ እጅግ ፡ ይበዛል እንዴት ፡ ሊነገር ፡ ይችላል በምን ፡ ሊገለጽ ፡ ይችላል ለእኔ ፡ ያለህ ፡ ፍቅር ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)