Loading
Singer
ተስፋ ፡ ሰጥቶኝ ፡ ሄደ ፡ የርስቴን ፡ መያዣ መንፈሱን ፡ ላከልኝ ፡ ለሕይወቴ ፡ ማደሻ የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ማግኛ ፡ መንገዱን አሳይቶኝ ፡ ሄዷል ፡ ለእኔ ፡ መሞቱን አዝ፦ ለእኔ ፡ መሞቱን ፤ ለእኔ ፡ መሞቱን (፬x) በምድር ፡ እስካለሁ ፡ እስካሁን ፡ ድረስ ሳዝን ፡ የሚያበረታኝ ፡ እምባዬን ፡ ሚያብስ በርስቴ ፡ መያዣ ፡ በታተምኩበት ዘለዓለም ፡ እኖራለሁ ፡ በእርሱ ፡ መጽናናት አዝ፦ ለእኔ ፡ መሞቱን ፤ ለእኔ ፡ መሞቱን (፬x) አሁን ፡ አውቄያለሁ ፡ የሚረባኝን በኑሮዬ ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ መሾም ፡ ያለብኝን የእኔ ፡ መጀመሪያ ፡ ብሎም ፡ መጨረሺያዬ ከምንም ፡ ከማንም ፡ በላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x) ዘላቂ ፡ ላልሆነው ፡ ለጊዜያዊው ፡ ደስታ እራሴን ፡ አላቀርብም ፡ ለሚያልቀው ፡ በዋይታ በመጠበቂያዬ ፡ ላይ ፡ እርሱን ፡ እጠብቃለሁ አይቀርም ፡ ይመጣል ፡ ጌታን ፡ አምነዋለሁ አዝ፦ ለእኔ ፡ መሞቱን ፤ ለእኔ ፡ መሞቱን (፬x) አሁን ፡ አውቄያለሁ ፡ የሚረባኝን በኑሮዬ ፡ ሁሉ ፡ ላይ ፡ መሾም ፡ ያለብኝን የእኔ ፡ መጀመሪያ ፡ ብሎም ፡ መጨረሺያዬ ከምንም ፡ ከማንም ፡ በላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x)