Loading
Singer
አዝ፦ ምድረ ፡ በዳዬ ፡ ለምልሟል (፪x) ኢየሱስ ፡ ዋጋ ፡ ከፍሎልኛል የዘላለም ፡ ኪዳን ፡ ገብቶልኛል የማይሻር ፡ ኪዳን ፡ ገብቶልኛል ፩) በልቤ ፡ ሲገባ ፡ የየሱሴ ፡ ፍቅሩ ሕይወቴ ፡ ተገዛ ፡ ጨከነ ፡ ለፍቅሩ ዛሬ ፡ በደስታ ፡ በአደባባይ ፡ ቆሜ ያድናል ፡ እላለሁ ፡ ደግሜ ፡ ደግሜ ኢየሱስ ፡ ጠበቃ ፡ ሆኖልኛል ከእንግዲህ ፡ የትኛው ፡ ያሰጋኛል ፪) ዛሬ ፡ ምን ፡ ይዋጠው ፡ ያክፉ ፡ ጠላቴ በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ሙሉ ፡ ነው ፡ ሕይወቴ ምክንያትን ፡ ፈላልጐ ፡ ዙሪያዬን ፡ ቢዞረው እኔ ፡ እንደው ፡ አልገኝ ፡ አጥሬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ ጠበቃ ፡ ሆኖልኛል ከእንግዲህ ፡ የትኛው ፡ ያሰጋኛል ፫) ሞትን ፡ ድል ፡ አድርጐ ፡ በተነሳው ፡ ጌታ እኔስ ፡ ተፈወስኩኝ ፡ ከሃጥያት ፡ በሽታ ዓለም ፡ ሰይጣን ፡ ሥጋ ፡ ዳግም ፡ ላያገኙኝ በጌታ ፡ በኢየሱስ ፡ ከሞት ፡ አመለጥኩኝ ኢየሱስ ፡ ጠበቃ ፡ ሆኖልኛል ከእንግዲህ ፡ የትኛው ፡ ያሰጋኛል