Loading
Singer
አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ እጮሀለሁኝ ፡ እኔ ፡ አልታክትም እስኪጎበኘኝ ፡ ተስፋ ፡ አልቆርጥም እንባዬን ፡ ካይኔ ፡ እስኪያብስልኝ እጠብቃለሁ ፡ እስኪደርስልኝ ፡ ጌታ ፡ እስኪያየኝ (፫x) አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ እስኪ ፡ እንደሀና ፡ እንባዬን ፡ ላፍስስ መሪር ፡ ሀዘኔን ፡ በፊቱ ፡ ልግለፅ ጨካኝ ፡ እንዳይደል ፡ እኔ ፡ አውቀዋለሁ ከእግሩ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ልማፀነው ፡ ደጅ ፡ ልጥናው (፫x) አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ ፈተናው ፡ በዝቶ ፡ ቢያዝለኝም ለሰይጣን ፡ ሀሳብ ፡ እጄን ፡ አልሰጥም እርዳኝ ፡ እላለሁ ፡ በፊቱ ፡ ሆኜ ድንቅ ፡ እንዲሰራ ፡ በእርሱ ፡ ታምኜ ፡ በረድኤቴ (፫x) አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ እታገሳለሁ ፡ ምልስ ፡ ይሆነኛል ጌታ ፡ ጨክኖ ፡ መች ፡ ይተወኛል የልመናዬ ፡ ፅዋዬ ፡ ሞልቶ ይጎበኘኛል ፡ በጊዜው ፡ መጥቶ ፡ በቃ ፡ ብሎ (፫x) አዝ፦ ለምን ፡ እንደዘገየ ፡ ለእኔ ፡ ባይገባኝም እጠብቀዋለሁ ፡ ፈፅሞ ፡ አይጥለኝም ስጋዬን ፡ ልንከስ ፡ ልማፀነው ፀሎቴን ፡ ሰምቶ ፡ እስኪመልሰው ፡ ጌታ