Loading
Singer
በጊዜያዊው ፡ ነገር ፡ ልቤ ፡ እንዳይሸነፍ በሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ነፍሴ ፡ እንዳትታለፍ ቃልህን ፡ በልቤ ፡ ሰውረው ፡ ጌታዬ ትዛዝህን ፡ ልጠብቅ ማስተዋል ፡ ይሁነኝ ፡ ወዳጄ ጥበብህ ፡ ትሁነኝ ፡ እህቴ (፪x) ያንተውማ ፡ ነገር ፡ ለምን ፡ ይይዘኛል የሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ለምን ፡ ያታልለኛል ከንቱውማ ፡ ነገር ፡ ለምን ፡ ይይዘኛል የሚያልፈው ፡ ነገር ፡ ለምን ፡ ያታልለኛል ለምን ፡ ለምን ፡ አሄሄ (፪x) ትላንትና ፡ የናቁትን ከንቱ ፡ ብዬ ፡ ያጥላላሁትን ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ ልወዳጀው ለምንድን ፡ ነው ፡ እንዲህ ፍቅር/ጓደኛ ፡ እምሆን (፪x) ባሞግስህ ፡ ደግሞ ፡ መልሶ ፡ ሲያሟግ ባከበርህ ፡ ደግሞ ፡ ሲያማርርብኝ ክፉ ፡ ደጉን ፡ ሁሉ ፡ እየተናገረ ይሄ ፡ አንደበቴ ፡ አንተን ፡ አስመረረ በአንደበቴ ፡ ላክብርህ ደስ ፡ የሚልህን ፡ ልናገርልህ (፪x) ያምራል ፡ ስባል ፡ ሞት ፡ ነው ፡ ብዬ ትናንትናን ፡ ንቄው ፡ ዘግቼው ፡ አልፌ ዛሬ ፡ ደግሞ ፡ ምን ፡ ተገኝቶ የናቁትን ፡ ማየት ፡ ኋላ ፡ ተመልሶ በአደባባይ ፡ ላይ ፡ ቆሜ ፡ ላመልክህ ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ ሆኜ ፡ በፊትህ ያልሆንኩትን ፡ ሆኜ ፡ በሰው ፡ ፊት ፡ ስታይ መጥፊያዬ ፡ እንዳይሆን ፡ የምልህ ፡ አለኝ በጓዳዬ ፡ ሆኜ ፡ ላክብርህ ሰው ፡ ያላየው ፡ ባህሪዬ ፡ ያስደስትህ በጓዳዬ ፡ ሆኜ ፡ ላክብርህ ድብቅ ፡ ገመናዬ ፡ ያስደስትህ እኔ ፡ በቃኝ (፪x) ፡ መሸነፍ ፡ በቃኝ እኔ ፡ በቃኝ (፪x) ፡ መታለል ፡ በቃኝ አዎ ፡ በቃኝ (፪x) ፡ መታለል ፡ በቃኝ አዎ ፡ በቃኝ (፪x) ፡ መሸነፍ ፡ በቃኝ በቃ ፡ በል ፡ እስቲ ፡ ጣልቃ ፡ ግባና ሁሉ ፡ የሚያምረው ፡ በአንተ ፡ ነውና በቃሽ ፡ በለኝ ፡ ጣልቃ ፡ ግባና ሁሉ ፡ የሚሳካው ፡ በአንተ ፡ ነውና