Loading
Singer
ስንቱ ፡ ያልተገባ ፡ ከፍታ ፡ ረግጧል ያልዘራዉን ፡ መልካም ፡ አጭዶ ፡ ተዘልሏል መንገዱ ፡ ተቃንቶለት ተሳክቶለታል ፡ በሕይወቱ ሳይለፋ ፡ ምንም ፡ ሳይደክም ባይተጋም ፡ ሙሉ ፡ ነዉ ፡ ቤቱ ለፃድቁ ፡ ተከለከለ ፡ በጽድቅ ፡ የዘራዉንም ፡ አጣ ሕይወቱ ፡ ከፋበት ፡ ተጨነቀ ፡ ያለ ፡ ኃጥያቱ ፡ ተቀጣ አላልፍልህ ፡ አለዉ ፡ ጨለማ ፡ መንጋቱን ፡ እየናፈቀ ጥሮ ፡ ግሮ ፡ አላተረፋም ፡ በኪሳራ ፡ ያለዉ ፡ አለቀ ለምን (፭x) ለምን ፡ ግን ለምን ፡ ለምን የኃይላቸዉ ፡ ጥንካሬ ፡ ብርታታቸዉ ፡ ሲበዛ በምስኪኑ ፡ ሲሳለቁ ፡ ሲያሳዩት ፡ ጭንቅ ፡ አበሳ አመፀኞች ፡ ከፍ ፡ ሲሉ ፡ ሳይደክሙ ፡ ሲከናወኑ ተከታይ ፡ ሲበዛላቸዉ ፡ ፃዲቁን ፡ ግን ፡ ሲኮንኑ ለምን (፭x) ለምን ፡ ግን ለምን ፡ ለምን እግዚአብሔር ፡ ከቶ ፡ አይባልም ፡ ለምን የሚሰራዉን ፡ ስለሚመዝን ፡ ፍርድ ፡ የተዛባ ፡ ቢመስልም ፡ እንኳን አላማ ፡ አለዉ ፡ የእርሱ ፡ ዝምታ ኃጥአን ፡ በድጥ ፡ ላይ ፡ ናቸዉ ይፈጥናል ፡ ዉድቀታቸዉ እግዚአብሄር ፡ ሲነሳ ፡ ከፊት ፡ ነዉ ፡ ጥፋታቸዉ ለልበ ፡ ንጹሐን ፡ ግን ፡ ቀን ፡ ይወጣላቸዋል የደረሰባቸዉን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተመልክቷል ፃድቅ ፡ ፃድቅ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፃድቅ እርሱ ፡ አይሳሳት ፡ ፃድቅ ፡ ነዉ ፡ ፃድቅ