Loading
Singer
እስከዛሬ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ኖሬ ፡ ተጉዤያለሁ ፡ ብዙ ፡ አብሬ አንዱ ፡ ሲሄድ ፡ አንዱ ፡ ሲመጣ ፡ አትለወጥ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ጥቁር ፡ አይል ፡ ፊትህ ፡ አይቀየር ፡ አትዘጋም ፡ የምህረትን ፡ በር ኧረ ፡ ስንቱ ፡ ጭንቁን ፡ እረስቶ ፡ እፎይ ፡ ብሏል ፡ አንተ ፡ ላይ ፡ ታምኖ (፪x) ያው ፡ ነህ (፰x) አልወደቅኩም ፡ በፈራሁት ፡ ላይ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ዓይን ፡ ዓይኖቼን ፡ ሲያይ ከእናት ፡ ከአባት ፡ ከወዳጅ ፡ ይልቅ ፡ ጠብቆኛል ፡ ክፉ ፡ ላይ ፡ እንዳልወድቅ ዞር ፡ አረገው ፡ ከፊቴ ፡ ቀድሞ ፡ ያንን ፡ ሃዘን ፡ ለእኔ ፡ አስቦ የተማሰው ፡ ጉድጓድ ፡ ተዘጋ ፡ በአንድ ፡ አፍታ ፡ ለሊቱ ፡ ነጋ (፪x) ያው ፡ ነህ (፰x) ብርድ ፡ አለ ፡ የሃሩሩ ፡ ጊዜ እንደ ፡ ህልም ፡ አለፈ ፡ የሃዘን ፡ ትካዜ (፪x) ትንግርት ፡ ነው ፡ የፍቅር ፡ ጉልበት ፡ ለወደቀው ፡ የደረሰለት የአለበት ፡ ጓዳ ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ ፡ አቁሞታል ፡ ዘይት ፡ ቀብቶ ሰው ፡ የለኝም ፡ በግራ ፡ በቀኝ ፡ ጉልበት ፡ ጠፋ ፡ አቅም ፡ አጣሁኝ ብሎ ፡ ለሚል ፡ ፍቅር ፡ አለው ፡ መላ ፡ ታሪክ ፡ ከፍቶ ፡ ያሳያል ፡ ሌላ የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የእኔ (የእኔ) የእኔ ፡ አባት ፡ ነህ ፡ የእኔ (የእኔ) የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነህ ፡ የእኔ (ኦኦኦ) የእኔ ፡ ጋሻ ፡ ነህ ፡ የእኔ (፪x) የእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ ፡ የእኔ (የእኔ) የእኔ ፡ አባት ፡ ነህ ፡ የእኔ (የእኔ) የእኔ ፡ ፍቅር ፡ ነህ ፡ የእኔ (ኦኦኦ) የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነህ ፡ የእኔ (፪x)