Loading
Singer
ጨለማ በሆነበት ብርሃንን የሚያበራ ስለ ከበረው ፀዳልህ ሚያወራ ሙት በገዛው ሸለቆ ሕይወትን የሚናገር ወደ ሞት ለሚነዱት ብርሃን የሚሆን የምሥራችን የሚያበስር ለክብርህ የሚሆን እቃ (3 ጊዜ) አርገኝ ጌታ ለክብርህ የማያሳፍር ክቡር ስምህን የሚሸከም ሙሉ ማንነቱን ላንተ የሚሰጥ ታማኝ ባርያ የማያሳፈር (2 ጊዜ) የወርቅ እቃ የምትለው በእሳትህ የነጠረ የምትሻውን ልታደርግበት ያማረ ሕያው ቅዱስ መስዋዕት አርጎ ራሱን የሰጠ ባለህበት አብሮ የሚኖር የማይርቅ እንዳስቀመጥከው የሚቀመጥ ለክብርህ የሚሆን እቃ . . . በዓለም ከሚታደለው ከጊዜያዊ ደስታ ሰማያዊውን ለመያዝ ልዘርጋ ዓለምን ነፍሴ ትጥላ በአይኖቼ ክብርን ትጣ በንቀት እያየኋት ላንት ልሩጥ ፍሬን ላፍራ አንትን ላኩራ ለክብርህ የሚሆን እቃ . . .