Loading
Singer
"ሚጡ ፡ ሚጡ ፡ ነይና ፡ አባባ ፡ እንቅልፋቸው ፡ ሳይመጣ ምከሩን ፡ እንበላቸው ፡ እንደትላንትና ። ውይ ፡ እኔ ፡ እኮ ፡ በጣም ፡ ነው ፡ ምወደው ፡ የሳቸውን ፡ ምክር ። እሺ ፡ ነይ ፡ ደስ ፡ ይለኛል አባባ ፡ አባባ? ምክር ፡ ምከሩን ፡ አባባ ። ምክር ፡ አላችሁ? አዎ ፡ አዎ ። እሺ ፡ እስቲ ፡ ዛሬ ፡ እስኪ ፡ ደግሞ ፡ ከምሳሌ ፡ መጽሃፍ እስቲ ፡ አንድ ፡ ምክር ፡ ልምከራቹህ ። አሺ ፡ እሺ ። እንደዚህ ፡ ይላል ፡ ልጆቼ ። ልጄ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ጠብቅ ትዕዛዜንም ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሸሽግ ትዕዛዜንም ፡ ጠብቅ ፡ በሕይወትም ፡ ትኖራለህ ፡ ያላል ። የእግዚአብሔርን ፡ ቃል ፡ ስትጠብቁ ፡ በሕይወት ፡ ትኖራላችሁ ፡ እሺ? እሺ! ፡ ጐበዝ ፡ ልጆች ። እስቲ ፡ እቼን ፡ መዝሙር ፡ ደስ ፡ እያላችሁ ፡ ዘምሯት ። እሺ ፡ አባባ ፡ ሚጡ ፡ ነይ! ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ስጠኝ ፡ እያላችሁ ፡ አምላክን ፡ ለምኑት ።" ልጄ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ጠብቅ ትዕዛዜንም ፡ በአንተ ፡ ዘንድ ፡ ሸሽግ ትዕዛዜን ፡ ጠብቅ ፡ በሕይወትም ፡ ትኖራለህ ህጌንም ፡ እንደ ፡ ዐይንህ ፡ ብሌን ፡ ጠብቅ በጣቶችህ ፡ ተሰራቸው ፡ በልብህ ፡ ጽላትም ፡ ጻፋቸው ጥበብን ፡ አንቺ ፡ እህቴ ፡ ነሽ ፡ በላት ማስተዋልንም ፡ ወዳጄ ፡ ብለህ ፡ ጥራት ልጄ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ጠብቂ ትዕዛዜንም ፡ በአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ሸሽጊ ትዕዛዜን ፡ ጠብቂ ፡ በሕይወትም ፡ ትኖሪያለሽ ህጌንም ፡ እንደ ፡ ዐይንሽ ፡ ብሌን ፡ ጠብቂ በጣቶችሽ ፡ ተሰራያቸው ፡ በልብሽ ፡ ጽላትም ፡ ጻፊያቸው ጥበብን ፡ አንቺ ፡ እህቴ ፡ ነሽ ፡ በያት ማስተዋልንም ፡ ወዳጄ ፡ ብለሽ ፡ ጥራያት ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ዕውቀትን ፡ ስጠኝ ጌታ ፡ ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ዕውቀትን ፡ ስጠኝ (ለእኔ) ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ዕውቀትን ፡ ስጠኝ ጌታ ፡ ጥበብ ፡ ማስተዋል ፡ ዕውቀትን ፡ ስጠኝ (ለእኔ)