Loading
ልጆች ፡ የእግዚአብሔር ፡ ስጦታዎች ፡ ናቸው [1] በጐ ፡ ስጦታና ፡ ፍፁም ፡ በረከት ከላይ ፡ ከብርሃናት ፡ አባት ፡ ዘንድ ፡ ይወርዳሉ [2] አዝ፦ ልጅ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አባት ፡ ልታደርገኝ የራስህን ፡ ፍቅር ፡ ልታስተምረኝ ገባኝ ፡ ነገሩ ፡ ውሎ ፡ ሳያድር ቀላል ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ ታላቅ ፡ ሚስጥር የአምላክ ፡ ስጦታ ፡ ልዩ ፡ በረከት በእናት ፡ ሆድ ፡ ተዋህዶ ፡ አጥንትና ፡ አጥንት ከሰው ፡ ሰው ፡ ስትፈጥር ፡ አንተ ፡ ለአንተ ፡ ክብር ከአይምሮ ፡ በላይ ፡ ነው ፡ ያሰኘኛል ፡ ተዓምር አዝ፦ ልጅ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አባት ፡ ልታደርገኝ የራስህን ፡ ፍቅር ፡ ልታስተምረኝ ገባኝ ፡ ነገሩ ፡ ውሎ ፡ ሳያድር ቀላል ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ ታላቅ ፡ ሚስጥር ተቀብያለሁ ፡ የእኔን ፡ ስጦታ የሰጠኸኝን ፡ በረከት ፡ ጌታ እንደ ፡ ወደድከኝ ፡ አየወደድኩህ ቤትህ ፡ እኖራለሁ ፡ እያመለኩህ እግዚአብሔር ፡ ያያል ፡ ጸሎቴን ፡ ይሰማል በባዕድ ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ፍሬያማ ፡ ያደርጋል በጐ ፡ ስጦታና ፡ ፍፁም ፡ በረከት ከአንተ ፡ ዘንድ ፡ ለእኔ ፡ ሆኗል ፡ የእኔ ፡ አባት አዝ፦ ልጅ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ አባት ፡ ልታደርገኝ የራስህን ፡ ፍቅር ፡ ልታስተምረኝ ገባኝ ፡ ነገሩ ፡ ውሎ ፡ ሳያድር ቀላል ፡ አይደለም ፡ ነው ፡ ታላቅ ፡ ሚስጥር ተቀብያለሁ ፡ የእኔን ፡ ስጦታ የሰጠኸኝን ፡ በረከት ፡ ጌታ እንደ ፡ ወደድከኝ ፡ አየወደድኩህ ቤትህ ፡ እኖራለሁ ፡ እያመለኩህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.