Loading
Singer
"ስለ ፡ ድሆች ፡ መከራ ፡ ስለ ፡ ችግረኞችም ፡ ጩኀት እግዚአብሔር ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ ፡ ይላል መድሃኒት ፡ አደርጋለሁ ፡ በላይ ፡ በላይ ፡ እገልጣለሁ" አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x) ተስፋ ፡ የሚያደርጉት ፡ የሚረዳቸው ከእኔ ፡ በስተቀር ፡ ማንም ፡ የላቸው . (1) . ፡ ተሞልተው ፡ ጠርተዉኛል ቶሎ ፡ ድረስልን ፡ ብለውኛል ያለቀሱትን ፡ ለቅሶ ፡ አይቻለሁ ጸሎታቸውን ፡ ሰምቼዋለሁ ከእንግዲህ ፡ ላይራቡ ፡ ልጆቼ ጥላ ፡ ባመጡላቸው ፡ እጆቼ አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x) መከራው ፡ በዝቶ ፡ ብዙ ፡ ተማረው ያለ ፡ ልክ ፡ አጥተው ፡ ተቸግረው ሞትን ፡ ሲመርጡ ፡ ከመኖር ፡ ይልቅ ያላቸው ፡ ሁሉ ፡ ተሟጦ ፡ ሲያልቅ በከንቱ ፡ ሲጨነቁ ፡ አየኋቸው እኔን ፡ የሚያክል ፡ ጌታ ፡ እያላቸው ስቃያቸውን ፡ አንጀቴ ፡ አልቻለም በቃ ፡ ብያለሁ ፡ ከእንግዲህ ፡ ሃዘን ፡ የለም አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x) ሁሉ ፡ እቋቸው ፡ ብቸኛ ፡ ሆነው የሚደርስልን ፡ ኧረ ፡ ማነው ወዳች ፡ ዘመዶቻቸው ፡ ሸሿቸው አናውቃችሁም ፡ ብለው ፡ ካዷቸው ያጥላሏቸውን ፡ አሳፍራለው እንደተናቁ ፡ መች ፡ አስቀራለው ወዮ ፡ ባሉበት ፡ አንደበታቸው ሰው ፡ ሁሉ ፡ ያያል ፡ ሳዘምራቸው አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x) እንጀራ ፡ ለአጡ ፡ መጋቢያቸው ፡ ነኝ ለተጠሙ ፡ ሁሉ ፡ የሚጠታ ፡ አለኝ ወዴኔ ፡ መጥተው ፡ ከቶ ፡ አያፍሩም የለመኑኝን ፡ አንዳች ፡ አያጡም ለጠሩኝ ፡ ሁሉ ፡ ባለጠጋ ፡ ነኝ የምስኪኖችን ፡ እምባ ፡ አባሽ ፡ ነኝ ሁሉን ፡ ሸለቆን ፡ መሙላት ፡ አውቃለሁ ችግረኞችን ፡ እባርካለው አዝ:- ለችግረኞች ፡ አሁን ፡ እነሳለሁ ማዳኔን ፡ ይዤ ፡ እገለጣለሁ የበረታውን ፡ ክንዴን ፡ ያያሉ በብዙ ፡ ብዙ ፡ ይባረካሉ (፪x)