Loading
Singer
አዝ፦ ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ የገርማል (፫x) ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ ይደንቃል (፫x) ንጹህ ፡ ልብን ፡ ስጠኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ እርሱ ፡ አለው ፡ ዋጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ እርሱ ፡ አለው ፡ ዋጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ ደንዳናውን ፡ ልቤን ፡ ስበር የከፉትን ፡ መውደድ የጠሉትን ፡ ማፍቀር ፡ ይልመድ ቂመኛውን ፡ ልቤን ፡ ፈውስ አሃሃሃ ፡ ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ይርዳኝ ፡ መንፈስህ አሃሃሃ ፡ እኔነቴ ፡ ጠፍቶ ፡ ይታይ ፡ አንተነትህ (፪x) አዝ፦ ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ የገርማል (፫x) ሰው ፡ ወዳጁን ፡ ቢወድ ፡ ይሄ ፡ ምን ፡ ይደንቃል (፫x) ንጹህ ፡ ልብን ፡ ስጠኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ እርሱ ፡ አለው ፡ ዋጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ ይቅር ፡ ባይ ፡ አድርገኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ልጠጋ እርሱ ፡ አለው ፡ ዋጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ ይቅር ፡ ማለት ፡ ሽንፈት ፡ ሆኖ ፡ ለእኔ የወንድሜ ፡ ጠላት ፡ ነፍሰ ፡ ገዳይ ፡ ሆኜ ፡ አይለቅ ፡ ዘመኔ ለፍርድ ፡ እንዳልበቃ ፡ ለኩነኔ (፪x) አሃሃሃ ፡ ፀጋህ ፡ ይደግፈኝ ፡ ይርዳኝ ፡ መንፈስህ አሃሃሃ ፡ እኔነቴ ፡ ጠፍቶ ፡ ይታይ ፡ አንተነትህ (፪x)