Loading
Singer
አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x) ተድላና ፡ ደስታ ፡ መጽናናት ፡ በረከት ሁሌ ፡ መንደላቀቅ ፡ በተሟላ ፡ ሕይወት እንደዚህ ፡ አይደለም ፡ እንዲህ ፡ አትመልከት ክርስትና ፡ አንዳንዴ ፡ መከራም ፡ አለበት አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x) የጨለማው ፡ ስልጣን ፡ ጥላውን ፡ ዘርግቶ ጠላት ፡ ኃይሉን ፡ ሲያሳይ ፡ እጅግ ፡ ተቆጥቶ በበትር ፡ ሲመታህ ፡ ሆምጣጤ ፡ ሲያጠጣህ በመስቀሉ መንገድ ፡ ወንድሜ ፡ አይክፋህ አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x) ማምለጫ ፡ ስትሻ ፡ ቀዳዳ ፡ ስትፈልግ ጭላንጭሉስ ፡ እንኳን ፡ ሲደፈን ፡ ሲመረግ በወህኒ ፡ ተጥለህ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲረሳህ የሕይወትህ ፡ ጌታ ፡ የሚረሳህ ፡ አይምሰልህ አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x) በምስራቹ ፡ ቃል ፡ በወንጌል ፡ ተሟገት ልብህ ፡ ሰፊ ፡ ይሁን ፡ አርቀህ ፡ ተመልከት ለማያልፈው ፡ ርስት ፡ ለአገርህ ፡ ተዋግተህ በላይ ፡ እንገናኝ ፡ ደምህን ፡ አጥለቅልቀህ አዝ፦ ልብህ ፡ ጽኑ ፡ ይሁን ፡ አትላላ ፡ ጠንክር በአመንክበት ፡ ጌታ ፡ በፍፁም ፡ አትፈር (፪x)