Loading
Singer
ባከብርህ ፡ ባመልክህ ፡ ባመሰግንህ ተባረክ ፡ ተወደስ ፡ ክበር ፡ እያልኩህ መቼ ፡ ይበቃኛል ፡ አንተን ፡ ሊገልጽህ ለእኔ ፡ ታደረከው ፡ ጌታ ፡ እየበዛብኝ በተከፋሁ ፡ ጊዜ ፡ ልቤ ፡ ሃዘን ፡ ሲውጠኝ አንተ ፡ ብቻ ፡ ለእኔ ፡ ፈጥነህ ፡ ደረስክልኝ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ሆነህ ፡ ነፍሴን ፡ እያጽናናህ ያንን ፡ ጨለማዬን ፡ በብርሃንህ ፡ አበራህ ስለዚህ ፡ ጌታዬ ፡ ወዳጄና ፡ አባቴ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ይህን ፡ ፍቅር ፡ ትቼ (፪x) በፊትህ ፡ ስበድል ፡ በአመጼ ፡ ስትቀጣኝ በበደሌ ፡ አዝኜ ፡ ፊትህን ፡ ላይ ፡ ስመኝ አይተህ ፡ አዘንክልኝ ፡ በንስሃ ፡ ሞልተህ ጽድቅን ፡ አወጣሃት ፡ ጠላቴን ፡ ረግጠህ ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ጉድለቴ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሙላቴ እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ቆሜያለሁ ሥምህን ፡ በዜማ ፡ አከብራለሁ (፪x) ይገርመኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ ይደንቀኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ (፪x) የዳንኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የቆምኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያጽናናኝ ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያስኬደኝ ፡ ሃሌሉያ ድካሜ ፡ ቢበዛ ፡ ጉድለቴ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ሙላቴ እንዲሁ ፡ በፀጋህ ፡ ቆሜያለሁ ሥምህን ፡ በዜማ ፡ አከብራለሁ (፪x) ይገርመኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ ይደንቀኛል ፡ ይሄ ፡ ፀጋ (፪x) የዳንኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የቆምኩበት ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያጽናናኝ ፡ ይሄ ፡ ፀጋ የሚያስኬደኝ ፡ ሃሌሉያ