Loading
Singer
ያላዩት ፡ አገር ፡ አይናፍቅም ፡ እንደሚሉት ፡ ሰዎች ተረት ፡ አይደለም ፡ ዓይኔ ፡ አይቶት ፡ ነው ፡ የልቦናዬ ሕይወቴን ፡ እንካ ፡ ኑሮዬን ፡ እንካ ፡ ብዬ ፡ የሰጠሁት ፡ ለዚህ ፡ ጌታዬ ዛሬም ፡ ፍቅሩ ፡ ያዘኝ ምህረቱ ፡ ያዘኝ ፀጋው ፡ ያዘኝ ያዘኝ (፭x) ያዘኝ (፬x) ላይተወኝ ፡ ቃል ፡ ገብቷል ፡ ላይጥለኝ የጌታዬ ፡ ፍቅሩ ፡ ማረከኝ (፪x) ሰላሙን ፡ ሞላ ፡ በቤቴ ተለወጠልኝ ፡ ሕይወቴ በቀኙ ፡ ደግፎ ፡ ያዘኝ መንፈሱ ፡ አሳረፈኝ አሁን ፡ አሁንማ (አሁንማ) ለሌላው ፡ አተረፈኝ ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ (፪x) ልዑል ፡ መጠጊያ ፡ ሆነኝ ፡ በክንፉ ፡ አሳረፈኝ ልቤ ፡ ከሥጋት ፡ አረፈ ፡ ጽዋዬ ፡ እየተረፈ (፪x) አሁን ፡ አሁንማ (አሁንማ) ለሌላው ፡ አተረፈኝ ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ (፪x) በጠላቶቼ ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ቀባኝ ፡ አምላኬ ፡ በዘይት ገመዴ ፡ ባማረ ፡ ስፍራ ፡ ወደቀች/ወድቃለች ፡ ልቤ ፡ እንዳይፈራ (፪x) አሁን ፡ አሁንማ (አሁንማ) ለሌላው ፡ አተረፈኝ ኢየሱስ ፡ ደረሰልኝ (፪x)