Loading
Singer
ላይጨልምብኝ ፡ አንዴ ፡ አብርቶት ፡ ጌታ ፡ ነገሩን ፡ ሁሉ ፡ ገልብጦ (፪x) ያለፈውን ፡ እንዳላስበው ፡ እንቅፋቶቹን ፡ አነሳሳቸው (፪x) ጨለማዬን ፡ አበራኸው ፡ እንደፈሳሽ ፡ አሳለፍከው : ጐህ ፡ ቀደደ ፡ ቀን ፡ ሊወጣ ፡ ማረፊያዬ ፡ ዘመን ፡ መጣ : መኖሪያዬ ፡ አንተ ፡ ሆንክልኝ ፡ ከጭንቀቴ ፡ አሳለፍከኝ/ገላገልከኝ (፪x) ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተባረክ (፪x) እስኪ ፡ ደጋግሜ ፡ ስምህን ፡ ልባርከው : እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ በዐይኔ ፡ ስላላየሁ ቀስቃሽ ፡ አልፈልግም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን ታሪክ ፡ ያለኝ ፡ ሰው ፡ ነኝ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር ፤ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር (፪x) ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (፪x) ከፊት ፡ ከፊቴ ፡ ጌታዬ ፡ ወጣና እሾሁን ፡ ሁሉ ፡ አነሳሳና (፪x) አደላደለው ፡ ሕይወቴ ፡ ቀና ይመራኝ ፡ ጀመር ፡ በድል ፡ ጐዳና (፪x) እረዳቴ ፡ ሆነህልኝ ፡ ተሸክመህ ፡ አሻገርከኝ አልነደፈኝ ፡ እባብ ፡ ጊንጡ : መች ፡ አገኘን ፡ እንደ ፡ ምኞቱ ከፍ ፡ ላድርግህ ፡ ቸር ፡ ጌታዬ ደስ ፡ ያሰኝህ ፡ ምሥጋናዬ (፪x) ተባረክ ፡ ጌታዬ ፡ ተባረክ ፤ ተባረክ ፡ ኢየሱሴ ፡ ተባረክ (፪x) እስኪ ፡ ደጋግሜ ፡ ስምህን ፡ ልባርከው እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ጌታ ፡ በዐይኔ ፡ ስላላየሁ ቀስቃሽ ፡ አልፈልግም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን ታሪክ ፡ ያለኝ ፡ ሰው ፡ ነኝ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር ፤ ከፍ ፡ በል ፡ እግዚአብሔር (፪x) ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ጌታ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ ከፍ ፡ በልልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (፪x) ያ ፡ ደመና ፡ እንዳያልፍ ፡ የለም ፡ ሲያስገመግም: ጠላቴም ፡ ሲለኝ ፡ የሚያድንህ ፡ የለም : ኧረዳቴ ፡ ግን ፡ እጁን ፡ ዘረጋ ፡ ከሰማያት እኔን ፡ ሊያወጣ ፡ ፈጥኖ ፡ ከሞት አንተ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ (፪x) ጌታ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ ኢየሱስ ፡ ስለእኔ ፡ ያልሆንከው ፡ ምን ፡ አለ ምን ፡ ልበልህ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ልበልህ ምን ፡ ልበልህ ፡ ጌታዬ ፡ ምን ፡ ልበልህ ምን ፡ ልክፈልህ ፡ ኧረ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ልክፈል