Loading
Singer
አዝ፦ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ፈልጋለሁ አትራቀኝ ፡ እልሃለሁ ተናገረኝ ፡ ሰማለሁ የአንተን ፡ ምሬት ፡ እሻለሁ (፪x) ከአገር ፡ ከወገን ፡ ተለይቼ ዘመድ ፡ አዝማድን ፡ ትቼ ያልከኝን ፡ ሁሉ ፡ ሰምቼ የገባህልኝ ፡ ተስፋ ፡ አይቼ አዝ፦ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ፈልጋለሁ አትራቀኝ ፡ እልሃለሁ ተናገረኝ ፡ ሰማለሁ የአንተን ፡ ምሬት ፡ እሻለሁ (፪x) አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ ፡ አላፈርኩም ተናግረኸኝ ፡ መቼም ፡ አልከሰርኩም በመንፈስህ ፡ ብርታት ፡ አግኝቼ አመልክሃለሁ ፡ ተደስቼ አዝ፦ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ፈልጋለሁ አትራቀኝ ፡ እልሃለሁ ተናገረኝ ፡ ሰማለሁ የአንተን ፡ ምሬት ፡ እሻለሁ (፪x) ጌታ ፡ ሕይወቴን ፡ አደስከው ተስፋዬን ፡ አለመለምከው ማጉረምረሜን ፡ ከእኔ ፡ ወሰድከው ሞቴንም ፡ በሕይወት ፡ ቀየርከው አዝ፦ ለአንተ ፡ መኖር ፡ ፈልጋለሁ አትራቀኝ ፡ እልሃለሁ ተናገረኝ ፡ ሰማለሁ የአንተን ፡ ምሬት ፡ እሻለሁ (፪x)