Loading
Singer
አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x) ፩) ግራ ፡ ቀኝ ፡ ለሚል ፡ ጭንቀት ፡ ለያዘው ፈውስን ፡ ፈልጐ ፡ በለቅሶ ፡ ላለው ደርሶ ፡ የሚፈውስ ፡ የሚታደገው ሁሉን ፡ የሚችል ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x) ፪) በገዢ ፡ ቁጣ ፡ ልቡ ፡ ለራደ ስፍራውን ፡ ሲለቅ ፡ ሸርተት ፡ ላለ የንጉሥ ፡ ልቡ ፡ በእጁ ፡ ይሆነው አጽንቶ ፡ የሚያቆም ፡ መድሃኒያለም ፡ ነው አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x) ፫) በባዕድ ፡ ምድር ፡ በእስር ፡ ላለ ተስፋዬ ፡ አሁንስ ፡ ማን ፡ ነው ፡ ለሚለው የእስራአኤል ፡ ብርታት ፡ ረዳት ፡ የሆነው እስረኛን ፡ ፈቺ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x) ፬) በሰማይ ፡ በምድር ፡ የሌለው ፡ መሳይ ለተዋረደ ፡ ክብርን ፡ የሚያሳይ እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ አረ ፡ ማን ፡ አለ ሁሉንም ፡ መስራት ፡ ማድረግ ፡ የቻለ አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x) ፭) እጅህ ፡ ስትሰራ ፡ ማየት ፡ ለጓጓው ተነስ ፡ እያለ ፡ ፊትህ ፡ ላነባው በእሳት ፡ መልሰህ ፡ ታሳየዋለህ ጠላቱን ፡ ጌታ ፡ ታሳፍራለህ አዝ፦ ለአንተ ፡ ጌታ ፡ አያቅትህም ለአንተ ፡ ፈውስም ፡ አይሳንህም (፪x)