Loading
Singer
ልትሰራ ፡ አስበህ ፡ ስትመጣ ፡ ወደ ፡ እኔ አንተ ፡ ያየኸውን ፡ ስታሳየኝ ፡ በዓይኔ ምህረትህ ፡ ሲለየኝ ፡ ለከበረው ፡ ሥራ ውስጤ ፡ ተደነቀ ፡ መገረም ፡ ተሞላ (፪x) ቆይ ፡ ምኔን ፡ ደስ ፡ ብሎ ፡ የቱስ ፡ እኔነቴ ወደ ፡ እኔ ፡ ያመጣህ ፡ ልታሰገባህ ፡ ወደ ፡ እኔ ይሄ ፡ አልበቃህ ፡ ብሎ ፡ በክብርህ ፡ እንድትሰራ ፍቅርህ ፡ የመረተኝ ፡ ባንተው ፡ እንድጠራ አዝ፦ ላምጣለህ ፡ ምሥጋና ፡ ልጨምር ፡ ዝማሬ ሕይወቴን ፡ ላዳንከው ፡ ከጨካኙ ፡ አውሬ ላምጣልህ ፡ ጭብጨባ ፡ ልጨምር ፡ ውዳሴ ለክብርህ ፡ ትዘምር ፡ ከሞት ፡ ተርፋ ፡ ነፍሴ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ብሎህ ፡ እንዲሁ ፡ የወደድከኝ ለሹመት ፡ ለክብር ፡ ብለህ ፡ የወሰንከኝ ኃጢአት ፡ ያጠፋህ ፡ ድካሜን ፡ የሻረከው ውልታህ ፡ በዝቶብኝ ፡ ፊትህ ፡ መጥቼአለሁ ይኸው ፡ አድናቆቴ ፡ ለክብርህ ፡ ምሥጋና ይኸው ፡ መገዛቴ ፡ ወደኸኛልና ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ የከንፈሬ ፡ ፍሬ ኧረ ፡ የአንተን ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ያበቃኝ ፡ ለዛሬ ልትሰራ ፡ አስበህ ፡ ስትመጣ ፡ ወደ ፡ እኔ አንተ ፡ ያየኸውን ፡ ስታሳየኝ ፡ በዓይኔ ምህረትህ ፡ ሲለየኝ ፡ ለከበረው ፡ ሥራ ውስጤ ፡ ተደነቀ ፡ መገረም ፡ ተሞላ (፪x) አዝ፦ ላምጣለህ ፡ ምሥጋና ፡ ልጨምር ፡ ዝማሬ ሕይወቴን ፡ ላዳንከው ፡ ከጨካኙ ፡ አውሬ ላምጣልህ ፡ ጭብጨባ ፡ ልጨምር ፡ ውዳሴ ለክብርህ ፡ ትዘምር ፡ ከሞት ፡ ተርፋ ፡ ነፍሴ ጌታ ፡ ሆይ ፡ በመንፈስህ ፡ እንጂ ፡ መች ፡ በብርታቴ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እስካሁን ፡ የሆነው ፡ በሕይወቴ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ሠላም ፡ ይሰማኛል ፡ ነገዬን ፡ ሳሰበው ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንደ ፡ በፊቱ ፡ አልሰጋም ፡ ተስፋዬ ፡ ፍቅርህ ፡ ነው አዝ፦ ላምጣለህ ፡ ምሥጋና ፡ ልጨምር ፡ ዝማሬ ሕይወቴን ፡ ላዳንከው ፡ ከጨካኙ ፡ አውሬ ላምጣልህ ፡ ጭብጨባ ፡ ልጨምር ፡ ውዳሴ ለክብርህ ፡ ትዘምር ፡ ከሞት ፡ ተርፋ ፡ ነፍሴ