Loading
የልቤ አምላክ ሁሉ ነገሬ እየመራኸኝ ባንተ ተምሬ ከራሴ መንገድ እየመለስከኝ ማይታለፈውን አሻገርከኝ ጌታ ምህረትህ እጅግ ብዙ ብዙ ነው ጌታ ምህረትህ አቤት ይቅርታህ እጅግ ብዙ ብዙ ነው አቤት ይቅርታህ አቤት ደግነትህ መጨረሻ የለው ለደግነትህ እርህራሔህ መጨረሻ የለው እርህራሔህ ላመስግንህ እስኪ ላመስግንህ ለውለታህ ምላሽ እንኳን ባይመጥንህ ላመስግንህ ውዴ ላመስግንህ ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንህ ከተጠመደብኝ ወጥመድ አስመልጠህ ከክፉ ውሳቤ ልቤን እኔን ጠብቀህ ቃልህን እየላክ አባ እየመከርከኝ ከጠላቴ አጥፊ እቅድ ፈጥነህ አዳንከኝ ተመስገን አባ ተመስገን ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንህ ተባረክ አባ ተባረክ ለውለታህ ምላሽ ምስጋናን ላብዛልህ በጭንቅ ቀኖቼ ሁሉ ከጎኔ ነህ ስብራቴን ሳካፍልህ መቼ ደከመህ ሁሉ በተወኝም ጊዜ የትም አልሄድህ በጊዜ ብዛት አይላላም ወዳጅነትህ ተመስገን አባ ተመስገን ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንህ ተባረክ አባ ተባረክ ለውለታህ ምላሽ ምስጋናን ላብዛልህ በምድረበዳ ሸለቆ አሰልጥነህ የጨከንክብኝ ሲመስለኝ ቀርበህ አባብለህ ሁሉ ለበጎ ሲቀየር በአይኔ እያየሁ ለመልካም ስላስጨነከኝ አከብርሃለው ተመስገን አባ ተመስገን ላረክልኝ ነገር እንኳን ባይመጥንህ ተባረክ አባ ተባረክ ለውለታህ ምላሽ ምስጋናን ላብዛልህ
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.