Loading
Singer
ምድርና ፡ ሞላዋን ፡ በቃልህ ፡ ያፀናህ በክብርህ ፡ ሞገስ ፡ በብርሃንህ ፡ ዓለምን ፡ የሞላህ እንዴት ፡ ላክብርህ ፡ ዛሬስ ፡ ምን ፡ ይዤ ፡ በፊትህ ፡ ልግባ አዲስ ፡ ምሥጋና ፡ አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ አይበዛብህምና አዝ:- እጆቼን ፡ ወደ ፡ ሰማይ ፡ አንስቼ በንጹህ ፡ ልብ ፡ ዛሬም ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም ላመስግነው ፡ አምላኬን ፡ በሰማይ ፡ ላለው ለኢየሱስ ፡ ቅኔ ፡ ልቀኝለት (፪x) ታማኝነቱንም ፡ ገናናነቱንም ፡ አይቼ ስለ ፡ ምሕረትህ ፡ ባስብ ፡ ባወራ ፡ አመታት ፡ ያጥሩኛል አቤቱ ፡ ኢየሱስ ፡ የታምራትህ ፡ ዘርፍ ፡ እረዝሟልና ለነፍሴ ፡ ዘወትር ፡ ተሟግተሃል ሕይወቴንም ፡ በደምህ ፡ ተቤዥተሃልና አዝ:- እጆቼን ፡ ወደ ፡ ሰማይ ፡ አንስቼ በንጹህ ፡ ልብ ፡ ዛሬም ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም ላመስግነው ፡ አምላኬን ፡ በሰማይ ፡ ላለው ለኢየሱስ ፡ ቅኔ ፡ ልቀኝለት (፬x) ታማኝነቱንም ፡ ገናናነቱንም ፡ አይቼ በላይ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ በክብር ፡ ነግሰህ ፡ ታየህ ፡ አቤቱ (፬x) (ክብር ፡ ይሁን) ላመስግነው ፡ አምላኬን በሰማይ ፡ ላለው ፡ ለኢየሱስ ቅኔ ፡ ልቀኝለት (፪x) በላይ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ በክብር ፡ ነግሰህ ፡ ታየህ ፡ አቤቱ (ክበር ፡ ክበር ፡ መድኃኒቴ) በላይ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ በክብር ፡ ነግሰህ ፡ ታየህ ፡ አቤቱ (ክበር ፡ ንገሥ ፡ መድኃኒቴ)(፪x) በላይ ፡ በዙፋንህ ፡ ላይ በክብር ፡ ነግሰህ ፡ ታየህ ፡ አቤቱ