Loading
Singer
አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው ላመስግነው የኃጢአቴን ፡ ቀንበር ፡ በላዬ ፡ ያለውን ሰበረው ፡ ከላዬ ፡ ቀና ፡ አደረገኝ ፡ ጌታዬ ቀደደው ፡ የመርገም ፡ ጨርቄን አራቀው ፡ ውዴ ፡ አበሳዬን አነጻኝ ፡ ጌታ ፡ በደሙ በልቤ ፡ ሞላ ፡ ሰላሙን ላመስግነው አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው ላመስግነው ዙሪያዬን ፡ ከቦኝ ፡ ጠላቴ ሚረዳኝ ፡ ባጣሁኝ ፡ ጊዜ በጭንቄ ፡ ሳለሁ ፡ ደረሰ እምባዬን ፡ ከዓይኔ ፡ አበሰ አሰበኝ ፡ ከአሪያም ፡ አምላኬ ጋሻዬ ፡ ሆነ ፡ ምርኩዜ ረገጠው ፡ ያስጨነቀኝን አሳደደው ፡ ያሳደደኝን ላመስግነው አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው ላመስግነው ምስቅልቅል ፡ ያለው ፡ ሕይወቴን የባዘነችውን ፡ ነፍሴን ኢየሱሴ ፡ ደርሶ ፡ አጣፈጠው መራራውን ፡ ኑሮ ፡ ለወጠው ሙሉ ፡ አደረገኝ ፡ ወዳጄ አወጣኝም ፡ ከኩነኔ ምን ፡ ልክፈለው ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ላክብረው ፡ ክብሬን ፡ በዕልልታ ላመስግነው አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው ላመስግነው ሰው ፡ የጠላውን ፡ ሃሳቢ የተገፋውን ፡ ሰብሳቢ ለቸገረው ፡ ፈጥኖ ፡ ደራሽ ለሚያነባ ፡ እምባውን ፡ አባሽ አንተ ፡ ነህ ፡ እውነተኛ ፡ ወዳጅ ማትለይ ፡ ሁሌም ፡ ማትሰለች ቢመኩብህ ፡ ታስመካለህ ኢየሱሴ ፡ አንተ ፡ ታኮራለህ ላመስግንህ አዝ፦ ላመስግነው ፡ ጌታን ፡ ላመስግነው ላመስግነው ፡ ውዴን ፡ ላመስግነው የረዳኝን ፡ ኢየሱስ ፡ ያገዘኝን ያቆመኝን ፡ አምላኬን ፡ ሰው ፡ ያደረገኝን ላመስግነው ፡ ዛሬም ፡ አቻም ፡ የለውም ቢያወድሱት ፡ እርሱስ ፡ ማይጠገብ ፡ ነው ላመስግነው