Loading
Singer
የህይወቴ ፡ እስትንፋስ ፡ በእጅህ ፡ መዳፍ ፡ ውስጥ ፡ ነው ፡ ያለው ያለ ፡ አንተ ፡ መኖር ፡ አልችልም ፡ በእርግጥ ፡ ሞቼ ፡ እቀራለሁ ህያውነቴ ፡ ባንተ ፡ ነው ፡ በነፍሴ ፡ ጌታ ለዘላለም ፡ ላመስግንህ ፡ ላዚም ፡ በእልልታ (፪x) ልባርክህ ፡ ልባርክህ ላምልክህ ፡ ላምልክህ (፪x) አዝ፦ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኝልሀለሁ ፡ እኔ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ ድምጼ ፡ ለአንተ ፡ ይሰማ (፪x) ከልቤ ፡ በሙሉ ፡ ሀይሌ (፪x) አመሰግንሀለሁ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ (፪x) ኢየሱስ (፪x) ኢየሱስ (፬x) አምላኬ ፡ አንተ ፡ ለእኔ ፡ መታመኛዬ ፡ አለቴ ደስታዬ ፡ አንተን ፡ ሳስብ ፡ ነው ፡ በእርግጥ ፡ ማረፍ ፡ መርካቴ ስለዚህ ፡ አንተን ፡ ላምልክህ ፡ ላውራ ፡ ክብርህን የዝማሬ ፡ ጽምፅ ፡ ይሰማ ፡ ላሸብሽብልህ (፪x) ከፍ ፡ ላርግህ ፡ ከፍ ፡ ላርግህ ላውድስህ ፡ ላወድስህ (፪x) አዝ፦ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኝልሀለሁ ፡ እኔ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ ድምጼ ፡ ለአንተ ፡ ይሰማ (፪x) ከልቤ ፡ በሙሉ ፡ ሀይሌ (፪x) አመሰግንሀለሁ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ (፪x) ኢየሱስ (፪x) ኢየሱስ (፬x) እንዳንተ ፡ የሚሆን ፡ ለእኔ ፡ አላገኘሁምና ከእናትም ፡ ከአባት ፡ ከወዳጅ ፡ በልጠህብኛልና አምላኬ ፡ መድሀኒቴ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ፈዋሼ በአምላኮ ፡ አንተን ፡ ማክበር ፡ ነው ፡ ምላሼ (፪x) ላመስግንህ ፡ ላመስግንህ ላሞጋግስህ ፡ ላሞጋግስህ (፪x) አዝ፦ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኝልሀለሁ ፡ እኔ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ ድምጼ ፡ ለአንተ ፡ ይሰማ (፪x) ከልቤ ፡ በሙሉ ፡ ሀይሌ (፪x) አመሰግንሀለሁ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ (፪x) ኢየሱስ (፪x) ማፍቀሬን ፡ ለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ጥልቅ ፡ የሆነ ፡ መውደዴን እገልፃለሁ ፡ ለስምህ ፡ ክብር ፡ በማቅረብ ፡ መስዋዕቴን ደጋግሜ ፡ አመልክሃለሁ ፡ ይህም ፡ ያንስሀል ያለምንም ፡ ዋጋ ፡ እንዲሁ ፡ አድነኽኛል (፪x) ልቀኝልህ ፡ ልቀኝልህ ላክብርህ ፡ ላክብርህ (፪x) አዝ፦ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ እቀኝልሀለሁ ፡ እኔ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ ፡ ድምጼ ፡ ለአንተ ፡ ይሰማ (፪x) ከልቤ ፡ በሙሉ ፡ ሀይሌ (፪x) አመሰግንሀለሁ ፡ ክብርን ፡ ለአንተ ፡ እሰጣለሁ (፪x) ኢየሱስ (፪x) ኢየሱስ (፬x)