Loading
Singer
የነፍሴ ፡ ቋንቋ ፡ ነህ ፡ (የሕይወቴ ፡ ዜና) ፪X ማወደስ ፡ የማደንቅ ፡ (የአንተን ፡ ልእልና)፪X ፡ የእኔ ፡ ተልእኮ ፡ ነው ፡ ጥሪና ፡ ውሳኔ እስትንፋሴ ፡ እስካለች ፡ ቀሪውን ፡ ዘመኔ ኢየሱስ ፡ ላድንቅህ ፬X በፏፏቴው ፡ ውበት ፡ (እጆችህ ፡ ባበጁት)፪X በተፈጥሮ ፡ ቀለም ፡ (ሁሉን ፡ ባቆነጁት)፪X ግርምቴም ፡ አይበቃ ፡ (ዝም ፡ አይልም ፡ አፌ)፪X ምሥጋና ፡ ይፈልቃል ፡ (ከመስክ ፡ ከደጃፌ)፪X የተፈጠርኩበት ፡ የምድር ፡ ላይ ፡ ኑሮ የተፃፈልኝም ፡ ሁሉም ፡ ተቀምሮ አንተን ፡ ማወደስ ፡ ነው ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ ማለት ጅማረው ፡ ፊፃሜ ፡ (የሕይወቴ ፡ መሠረት)፪X የነፍሴ ፡ ቋንቋ ፡ ነህ ፡ (የሕይወቴ ፡ ዜና) ፪X ማወደስ ፡ የማደንቅ ፡ (የአንተን ፡ ልእልና)፪X ፡ የእኔ ፡ ተልእኮ ፡ ነው ፡ ጥሪና ፡ ውሳኔ እስትንፋሴ ፡ እስካለች ፡ ቀሪውን ፡ ዘመኔ ኢየሱስ ፡ ላድንቅህ ፬X የሰማዩ ፡ ቀለም ፡ (የአድማሳቱ ፡ ግርማ)፪X የንፋሱ ፡ ፉጨት ፡ (የአዋፋቱ ፡ ዜማ) ፡ ፪X ክብርህን ፡ መናገር ፡ (ውዳሴን ፡ ማሳረግ)፪X ዝናህን ፡ መተረክ ፡(ከፍ ፡ ከፍ ፡ ማድረግ)፪X የተፈጠርኩበት ፡ የምድር ፡ ላይ ፡ ኑሮ የተፃፈልኝም ፡ ሁሉም ፡ ተቀምሮ አንተን ፡ ማወደስ ፡ ነው ፡ ክበር ፡ ክበር ፡ ማለት ጅማረው ፡ ፊፃሜ ፡ (የሕይወቴ ፡ መሠረት)፪X