Loading
Singer
ሕይወት ፡ እንደ ፡ ጥላ ፡ ሲያልፍ ውበት ፡ እንደ ፡ ቅጠል ፡ ሲረግፍ ያመኑበት ፡ ወዳጅ ፡ ሲከዳ ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ሆኜ ፡ ልጐዳ አዝ፡- ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል (፪x) ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል አክሊል ፡ ከምደፋ ፡ በዓለም የኢየሱስን ፡ መስቀል ፡ ልሸከም ሰይጣን ፡ ከሚያቆላምጠኝ ኢየሱሴ ፡ በእግሩ ፡ ይርገጠኝ አዝ፡- ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል (፪x) ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል ዙሪያዬን ፡ አጅቦኝ ፡ ወታደር በቄሳር ፡ ሰገነት ፡ ከማደር ደም ፡ እንባ ፡ እያፈሰስኩ ፡ ለጌታ ይሻለኛል ፡ ለእኔስ ፡ ጐልጐታ አዝ፡- ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል (፪x) ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል በረደኝ ፡ አልልም ፡ ከንግዲህ ራበኝ ፡ ጠማኝ ፡ አልል ፡ ከንግዲህ አፌን ፡ በአፈር ፡ ውስጥ ፡ ቀብሬ እኖራለሁ ፡ ቃሌን ፡ አክብሬ አዝ፡- ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል (፪x) ከኢየሱስ ፡ ጋር ፡ ኑሮ ፡ ይሻለኛል