Loading
Singer
"ፍቅር ፡ ጌታ ፡ ጌታ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ አንተ ፡ ብቻ አንተ ፡ ብቻ" አዝ:- ከወደድኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልውደድህ ካፈቀርኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ላፍቅርህ ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ የአንተ ፡ ፍቅር ፡ እንከን ፡ የሌለበት አሳልፎ ፡ ነፍስን ፡ እስከ ፡ መስጠት ከዚህ ፡ ዕውቀት ፡ መማር ፡ እንኳን ፡ ባልችል እኔ ፡ አፍቅሬ ፡ አይቻለሁ ፡ በምድር አዝ:- ከወደድኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልውደድህ ካፈቀርኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ላፍቅርህ ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ ሰው ፡ ስጥተኀኝ ፡ ወድጄ ፡ ከልቤ ስገልጥለት ፡ ፍቅሬን ፡ በስራዬ ሚከፈለውን ፡ ዋጋ ፡ ከፍያለሁ በሕይወቴ ፡ ብዙ ፡ አሳልፊያለሁ አዝ:- ከወደድኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልውደድህ ካፈቀርኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ላፍቅርህ ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ ፍቅር ፡ ማለት ፡ እራስን ፡ መስጠት ፡ ነው ለወደዱት ፡ ታማኝ ፡ መሆን ለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ፍቅር ፡ ስፈትሸው ወድሃለሁ ፡ ምለው ፡ ውሸቴን ፡ ነው አዝ:- ከወደድኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልውደድህ ካፈቀርኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ላፍቅርህ ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ ምላሽ ፡ መስጠት ፡ ለአንተ ፡ ለፍቅርህ ፡ ሚሆን ከወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ ላቅርብልህ ፡ ምላሽ አንደበቴ ፡ በጣም ፡ እንደምወድህ ቢመሰክር ፡ ውዴ ፡ ማሬ ፡ ብልህ ምን ፡ ይጠቅማል ፡ ቃላት ፡ ብደረድር ተግባር ፡ የለሽ ፡ ከሆነ ፡ የኔ ፡ ፍቅር አዝ:- ከኖርኩልህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልኑርልህ ከመሰልኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልምሰልህ ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ ከአፌ ፡ የሚወጣው ፡ ክሽን ፡ ያለ ፡ ያማረ ስራዬ ፡ የዓለም ፡ ድኖ ፡ እንዳልዳነ የእውነት ፡ ብወድህ ፡ ይሄ ፡ ይለውጠኛል ቃሌን ፡ ከተግባሬ ፡ አንድ ፡ አድርግልኝ አዝ:- ከኖርኩልህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልኑርልህ ከመሰልኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልምሰልህ ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ አንተ ፡ ትቀጣለህ ፡ ሃይለኛ ፡ ነህ ፡ ብዬ እሳት ፡ እንዳልጣል ፡ ሲኦልን ፡ ፈርቼ ይህን ፡ አልፈልግም ፡ ባፈቅርህ ፡ በቂ ፡ ነው ላፈቀሩት ፡ መኖር ፡ አይከብድም ፡ ቀላል ፡ ነው አዝ:- ከኖርኩልህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልኑርልህ ከመሰልኩህ ፡ የእውነቴን ፡ የእውነቴን ፡ ልምሰልህ ቃሌ ፡ ሌላ ፡ ተግባር ፡ ሌላ ፡ አይሁንብህ የምትወደኝ ፡ ጌታ ፡ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ አንዴ ፡ ወደኀኛል ፡ በዘለዓለም ፡ ፍቅርህ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ የልቤ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ የነፍሴ ፡ ወዳጅ ፡ ነህ