Loading
Singer
አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x) ስራብ ፡ እያበላኝ ፡ ስጠማ ፡ እያጠጣኝ ጉዴን ፡ ገመናዬን ፡ እየሸፈነልኝ ምን ፡ ጐደለህ ፡ እያለ ፡ ሌት ፡ ተቀን ፡ ያየኛል የድሃ ፡ አደግ ፡ አባት ፡ እግዚአብሔር ፡ ወዶኛል አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x) ልቤን ፡ የጣልኩበት ፡ ተስፋ ፡ የማደርገው ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ ዛሬም ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው ብድራት ፡ ፊቴ ፡ አለ ፡ የተዘጋጀልኝ ማንም ፡ አይወስደውም ፡ ኢየሱስ ፡ እያለልኝ አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x) እንዳለፈ ፡ ውኃ ፡ ችግሬን ፡ አስረሳኝ የማይቻለውን ፡ አስችሎ ፡ አሳለፈኝ ሰላሙ ፡ በዛልኝ ፡ ሃዘኔ ፡ ተረስቷል በእግዚአብሔር ፡ በአምላኬ ፡ ደስታዬ ፡ ጨምሯል አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x) ከማር ፡ ይልቅ ፡ ጣፍጦ ፡ አየሁት ፡ ኑሮዬን እጅግ ፡ አከበርኩት ፡ ቸሩ ፡ መድኃኒቴን በለመለመ ፡ መስክ ፡ ሁሌ ፡ ያሰማራኛል የበረከት ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ባርኮኛል አዝ፦ ከወደደ ፡ አይለቅም ፡ ይጣፍጣል ፡ ፍቅሩ ደስታ ፡ በደስታ ፡ ነው ፡ ከእርሱ ፡ ጋር ፡ መኖሩ (፪x)