Loading
Singer
ምህረትህ ፡ ጌታዬ ፡ ምህረትህ ምህረትህ ፡ አምላኬ ፡ ምህረትህ ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ ነው ለዚህ ፡ መድረሴ (፬x) ምህረትህ ፡ እንዴት ፡ በዝቷል ከፍ ፡ ብሏል ፡ ለእኔስ ፡ ገኗል (፪x) በበደሉ ፡ ምክንያት ፡ ጠፍቶ ፡ የነበረው ፡ ሰው ከጥፋት ፡ ጐዳና ፡ በፍቅርህ ፡ መለስከው የክህነቱን ፡ ስራ ፡ ኑሮው ፡ አድርጐታል ያዳነውን ፡ አምላኩን ፡ ሁሌ ፡ ይቀድሰዋል (፪x) ምህረትህ (፬x) ፡ ለእኔ ፡ በዝቷል ምህረትህ (፬x) ፡ ለእኔ ፡ በዝቷል ብብዙዎችም ፡ መካከል (አመሰግንሃለሁ) ቸርነትህ ፡ ምድርን ፡ ሞልቷል (እዘምረዋለሁ) የስምህ ፡ ትርጉም ፡ ገብቶኛል (ሁሌ ፡ እጠራዋለሁ) ብብዙዎችም ፡ መካከል (አመሰግንሃለሁ) ቸርነትህ ፡ ምድርን ፡ ሞልቷል (እዘምረዋለሁ) ኢየሱስ ፡ ማለት ፡ ገብቶኛል (ሁሌ ፡ እጠራዋለሁ) ንጉሥ ፡ ንጉሥን ፡ ሲሽረው ኃያል ፡ ኃያሉን ፡ ሲያወርደው ጊዜው/አንዱ ፡ ሲያልፍ ፡ ሲተካ ፡ በሌላ ፡ ጌታ ኢየሱስ ፡ ግን ፡ ሁሌ ፡ የጌቶች ፡ ጌታ (፪x) አይቼዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ እኔም ፡ በኑሮዬ ፡ አሃሃ አመታት ፡ አለፉ ፡ አላለፈም ፡ ጌታዬ አይቼዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ እኔም ፡ በኑሮዬ ፡ አሃሃ ዘመናት ፡ አለፉ ፡ አላለፈም ፡ ጌታዬ አይቼዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ እኔም ፡ በኑሮዬ ፡ አሃሃ ኃያላን ፡ አለፉ ፡ አላለፈም ፡ ጌታዬ አይቼዋለሁ ፡ ኦሆሆ ፡ እኔም ፡ በኑሮዬ ፡ አሃሃ ብዙዎች ፡ አለፉ ፡ አላለፈም ፡ ጌታዬ ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ ጠዋት ፡ ማታ አመልከዋለሁ ፡ ይህን ፡ ጌታ (፪x) ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ ጠዋት ፡ ማታ ሾመዋለሁ ፡ በከፍታ (፪x) ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ ሁሌ ፡ ማታ አስበዋለሁ ፡ በመኝታ (፪x) ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ ጠዋት ፡ ማታ እደነቃለሁ ፡ በዚህ ፡ ጌታ (፪x)