Loading
Singer
አንተ ፡ አገልጋይ ፡ ጌታን ፡ የምትወደው በድካም ፡ ሕይወት ፡ ያለኸው ከሸለቆ ፡ ውጣ ፡ ና ፡ ና ዛሬም ፡ ኢየሱስ(ጌታ) ፡ ይወድሃልና ይጠራሃልና እርሻውን ፡ አርሰህ ፡ ጐልጉለህ ፡ለመከሩ ፡ ደክመህ ስለወንጌል ፡ ብለህ ፡ ብዙ ፡ ዋጋ ፡ ከፍለህ (አሁን ፡ ምነው ፡ ደከምህ ፡ አዝመራው ፡ ሲቃረብ የዚች ፡ ዓለም ፡ ፡ ፡ ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ አያልቅም ) (፪x)፡ ፡ ፡ አዝ አንተ ፡ አገልጋይ ተስፋ ፡ አይቆረጥ ፡ በጌታ ፡ ምህረቱ ፡ ብዙ ዓለም ፡ አድክማቸው ፡ ለደነዘዙ ፡ ፡ ፡ (የደከመን ፡ ጉልበት ፡ እንደ ፡ ንስር ፡ ያድሳል ወደ ፡ ቀደመው ፡ክብር ፡ ዳግም ፡ ይመልሳል) (፪x) አዝ አንተ ፡ አገልጋይ ዘመኑ ፡ ሲቃረብ ፡ ክፉንም ፡ ዙሪያህ ሰው ፡ የላዩን ፡ ትቶ ፡ የምድሩን ፡ ያስባል (ነገር ፡ ግን ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ንፋስን ፡ መከተል የከበረው ፡ብድራት ፡ ኢየሱስን ፡ ማገልገል) ፡ (፪x) አዝ አንተ ፡ አገልጋይ ወንድሜ ፡ ሆይ ፡ ስለምን ፡ ተስፋ ፡ ቆረጥክ ፡ ጌታ ፡ እኮ ፡ ይወድሃል ያውም ፡ እስከ ፡ መስቀል ፡ ሞት ፡ ዛሬ ፡ ና ፡ ተነስ ፡ ጌታ ፡ ሳይመጣ አገልግለው አንተ ፡ መስክረህላቸው ፡ ያስተማርካቸው ዛሬ ፡ አድገው ፡ ቤቱ ፡ አገልጋዮች ፡ ናቸው (ዘወትር ፡ በጌታ ፡ ፊት ፡ ይጸልዩልሃል እግዚአብሔርም ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ አንተን ፡ ያስብሃል) (፪x) እግዚአብሔር ፡ እንደ ፡ ሳምሶን ፡ አንዴ ፡ ያስብሃል