Loading
Singer
አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝhttps://play.google.com/store/apps/details?id=com.atpc የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ (፪x) የበደሌን ፡ ብዛት ፡ አይተህ ፡ አልሄድክም ፡ ፊትህን ፡ አዙረህ ይቅርታህ ፡ ለእኔም ፡ ደርሶኛል ፡ . (1) . ፡ አስጀምረኸኛል እራራህልኝ ፡ ጌታዬ ፡ ለድካሜ ፡ ማረፊያዬ ለርሃቤ ፡ ነህ ፡ ጥጋቤ ፡ ለጥማቴ ፡ እርካታዬ አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝ የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ሌት ፡ ተቀን ፡ ሥምህን ፡ ስጠራ ፡ ድንቃ ፡ ድንቅህን ፡ ሳወራ የሰራህልኝን ፡ ተዓምር ፡ ውለታህን ፡ ስመሰክር ቢመሽ ፡ ቢነጋ ፡ አልሰለችም ፡ ክብሬ ፡ ነህ ፡ አላፍርብህም ቆርሼ ፡ መብላት ፡ የቻልኩት ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ እንጀራ ፡ ያገኘሁት አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝ የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ ግራ ፡ ቀኙን ፡ እየማተርኩ ፡ የሚረዳኝ ፡ እየፈለኩ አንተን ፡ አገኘሁ ፡ መልካሙን ፡ የሚባርክ ፡ ምስኪኑን ወጣሁኝ ፡ ከምድረበዳ ፡ ለምለም ፡ ደረቁ ፡ ጓዳ ቀና ፡ ሆነልኝ ፡ መንገዱ ፡ በቃ ፡ ለኑሮ ፡ መሰደዱ አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝ የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ እኔን ፡ ደካማውን ፡ መርጠህ ፡ ብልሹነቴን ፡ ለውጠህ ውዳቂ ፡ የተጣልኩትን ፡ ሰው ፡ ይገርማል ፡ እንዴት ፡ ወደድከው ይብዛልህ ፡ ይኸው ፡ ምሥጋናዬ ፡ ዝማሬ ፡ ሆታ ፡ ዕልልታዬ በብዙ ፡ እረፍት ፡ ያሳረፍከው ፡ ኧረ ፡ እንደ ፡ እኔ ፡ የኮራ ፡ ማነው አዝ፦ ከሰው ፡ ልጆች ፡ ይልቅ ፡ ውበትህ ፡ ሆ ፡ አማረኝ የአንተ ፡ መሆኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ (፪x)