Loading
Singer
አዝ፦ ክንዱ ፡ ነው ፡ ታሪኬን ፡ የለዋወጠው ጣቱ ፡ ነው ፡ ነገሬን ፡ የቀያየረው (፪x) አይቻለሁ ፡ በአንተ ሸለቆው ፡ ውኃ ሲሞላ ጌታ ፡ ስትሆነኝ ፡ ከለላ (፪x) አንገት ፡ እንድደፋ ፡ እንዳቀረቅር ከሰው ፡ በታችን ፡ ሆኜ ፡ ነበር ፡ ምኞቱ ጠላቴማ ፡ ሰው ፡ ለማድረግ ፡ ከንቱ ፡ አወይ ፡ ልፋቱ የማመልከው ፡ ጌታ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ እንደገና ፡ አነሳኝ ፡ ዳግም ፡ አቆመኝ ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ እኮ ፡ ማነው ፡ ማነው እሃሃሃ ፡ እግዚአብሔር ፡ እኮ ፡ ነው ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x) አዝ፦ ክንዱ ፡ ነው ፡ ታሪኬን ፡ የለዋወጠው ጣቱ ፡ ነው ፡ ነገሬን ፡ የቀያየረው (፪x) አይቻለሁ ፡ በአንተ ሸለቆው ፡ ውኃ ሲሞላ ጌታ ፡ ስትሆነኝ ፡ ከለላ (፪x) በዚያ ፡ በጭንቅ ፡ ቀን ፡ በቁርጥ ፡ ጊዜ ፡ በመከራ ፡ ሰዓት ከጐኔ ፡ የሚቆም ፡ አይዞህ ፡ የሚለኝ ፡ አጋዥ ፡ ባጣሁበት የናዝሬቱ ፡ ኢየሱስ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ ሲመጣ ጉልበቴም ፡ ከፍ ፡ አለልኝ ፡ አቅሜም ፡ በረታ ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ ኧረ ፡ ማነው ፡ ማነው ማነው ፡ ማነው ፡ ማነው ፡ እኮ ፡ ማነው ፡ ማነው እሃሃሃ ፡ እግዚአብሔር ፡ እኮ ፡ ነው ለእኔ ፡ የደረሰው (፪x)