Loading
Singer
አበቃ ፡ አከተመ ፡ አይሆንም ፡ በተባለበት የጌታ ፡ ስም ፡ ሲጠራ ፡ ሁሉ ፡ ይዘራል ፡ ህይወት ያለአንዳች ፡ እርዳታ ፡ ብቻውን ፡ ድንቅን ፡ አድርጐ ልጆቹን ፡ ያሣርፋል ፡ በሀይሉ ፡ ተገለጦ ታላቅነቱ ፡ አይወሰን ፡ ከ ፡ እስከ ፡ አይባልም ብቻ ፡ እርሱ ፡ ይስራ ፡ እንጂ ፡ ማንም ፡ ፊቱ ፡ አይቆምም (፪x) አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x) የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x) ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x) ጽኑ ፡ ግንብ ፡ በጠላት ፡ ፊት ፡ የማይደፈር ፡ መከታ ከክፋት ፡ ከሰይጣን ፡ እጅ ፡ የሚከልል ፡ ጌታ ነው ፡ እኛ ፡ ምናመልከው ፡ ሀይለኛና ፡ ባለስልጣን ተጠግተነው ፡ አርፈናል ፡ መደገፊያ ፡ ሆኖልን ጥበቃው ፡ እጅግ ፡ ያስደንቃል ፡ ልጆቹን ፡ ያሳርፋል ሀይሉም ፡ ከቶ ፡ አይደክምም ፡ በሰልፍ ፡ ይበረታል (፪x) አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x) የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x) ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x) ጌታ ፡ ከርሱ ፡ ጋር ፡ የሆነ ፡ ኽረ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ ያሻዋል ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ ሆኖ ፡ ተማምኖ ፡ ይኖራል በክፉ ፡ ቀን ፡ አይሰጋም ፡ አምላኩ ፡ ይታደገዋል ከረግረግ ፡ ከጭቃ ፡ አውጥቶ ፡ በአለት ፡ ያቆመዋል ዛሬም ፡ ይህ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ካለ ፡ ምንደነው ፡ የሚያስፈራን በእርሱ ፡ እየተማመንን ፡ በድል ፡ እንሄዳለን (፪x) አዝ፦ ጌታችን ፡ ክንደብርቱ ፡ ነው (፫x) የለም ፡ ሚገዳደረው ፡ አርሱ ፡ ብርቱ ፡ ነው ኢየሱስ ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፫x) ማነው ፡ የሚቋቋመው ፡ አሸናፊ ፡ ነው (፪x) ከጌታ ፡ የተነሳ ፡ በህይወት ፡ መኖር ፡ ችለናል ካስጨናቂዎቻችን ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ አርፈናል ማዳኑን ፡ የክንዱን ፡ ብርታት ፡ ባይናችን ፡ አሣይቶናል ስለዚህም ፡ ልናከብረው ፡ ወደ ፡ እርሱ ፡ መጥተናል ለክበሩ ፡ እንዘምራለን ፡ እናመሰግነዋለን ጌታ ፡ ስለሚገባው ፡ እናመልከዋለን (፪x) ምስጋና ፡ ለርሱ ፡ ይገባዋል (፫x) ሌላ ፡ ምን ፡ ይሰጠዋል ፡ ለርሱ ፡ ይገባዋል (፬x)