Loading
Singer
Updated 9h ago
በዓለም ፡ ፍቅር ፡ እንዳልነደፍ ከሚጠፉት ፡ ጋር ፡ እንዳልሰለፍ አረማመዴን ፡ አቅናውና የራስህ ፡ አድርገኝ ፡ ቀይረኝና ከሚጠፉት ፡ እንዳልሆን ፡ ጠብቀኝ:: ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አብዛልኝ (፪x) አንተ ፡ የሌለህበት የዓለም ፡ ዝና ፡ የዓለም ፡ ዕውቀት ኢሄ ፡ ሁሉ ፡ ከንቱ ፡ ነዉ ንፋስን ፡ እንደመከተል ፡ ነው ከሚጠፉት ፡ እንዳልሆን ፡ ጠብቀኝ:: ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አብዛልኝ (፪x) በአንደበቴ ፡ እንዳልረክስ ወንድሜንም ፡ እንዳልተነኩስ አቤቱ ፡ ማስተዋልን ፡ ስጠኝ መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ና ፡ አስተምረኝ ከሚጠፉት ፡ እንዳልሆን ፡ ጠብቀኝ:: ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አብዛልኝ (፪x) ዓይኔን ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እንዳቀና መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ናልኝና ፈውሰኝ ፡ ቀድሰኝ መጠቀሚያ ፡ ገንዘብህ ፡ አድርገኝ ከሚጠፉት ፡ እንዳልሆን ፡ ጠብቀኝ:: ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አብዛልኝ (፪x)