Loading
Singer
ከመወለዴ ፡ ጀምሮ ፡ የማውቀው ፡ መልካም ፡ አንድ ፡ ነው ከልጅነቴ ፡ ጀምሮ ፡ የማውቀው ፡ መልካም ፡ አንድ ፡ ነው እርሱም ፡ አንተን ፡ ነው (፫x) ጌታ ፡ መልካም ፡ ነው አምላኬ ፡ አምላኬ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ማነው (፪x) ኢየሱስ ፡ ሥልጣንህ ፡ ገደብ ፡ የለው ኢየሱስ ፡ መንግሥትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለው በዙፋንህ ፡ ፀንተህ ፡ ጥንትም ፡ ነበርክ ዛሬም ፡ በክብር ፡ አለህ ለዘለዓለም ፡ ደግሞ ፡ በሥልጣንህ ገና ፡ ትኖራለህ ከሁሉም በላይ ነህ የኔ ጌታ፣ ሁሉን ትገዛለህ የሚወዳደርህ አቻ የለህ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ አምላኬ አምላኬ እንዳንተ ….. ሰምቼ ፡ ነበረ ፡ በጆሮዬ :ጌታ ማዳንህን ለብዙዎች ፡ ጥላ ፡ የማምለጫ ፡ አለት ፡ መሆንህን በእውነትም ፡ አዳኝ ፡ ነህ ፡ መድሃኒቴ እኔም ፡ አይቻለሁ ፡ ከዚህ ፡ ከጨለማ ከሞት ፡ መንደር ፡ በአንተ ፡ አምልጫለሁ ጌታ እንዳንተ መልካም፣ ጆሮዬም አልሰማም፣ ጌታ እንዳንተ መልካም፣ አይኖቼም አላዩም፣ ጌታ እንዳንተ መልካም፣ ከቶ አልገጠመኝም፣ ለዘላለም ክበር፣ ከፍ በልልኝ(፪x) እንዳንተ የሚሆን ለኔ የለም፣ አንተ ልዩ ከሁሉ ከላይ ነህ፣ አልፋና ኦሜጋ የኔ ጌታ፣ ዘላለም በክብር ምትበረታ አልፋና ኦሜጋ አቻ የለህ ዘላለም በክብር ትኖራለህ ከመወለዴ ፡ ጀምሮ ….