Loading
Singer
አዝ፦ ከምንጩ ፡ ስለቀዳሁ ፡ ስለጠጣሁ ፡ ስለረካች ፡ ነፍሴ ምህረት ፡ ስላገኘሁ ፡ አቀርባለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ በደሙ ፡ ስለዋጀኝ ፡ ስላዳነኝ ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ ለኪዳኑ ፡ ስላሰበኝ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጌታዬን ፡ ስባርክ ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ መድህኔ ስላዳነኝ ፡ ከሞት ፡ ከኩነኔ ሥሙ ፡ ይክበር ፡ የጸዮኑ ፡ አለት ተቆረጠ ፡ የኀጢአት ፡ ሰንሰለት ለቤዛ ፡ ቀን ፡ በእርሱ ፡ ታትሜያለሁ በመንፈሱ ፡ ልደት ፡ አግኝቻለሁ ሠማያዊ ፡ ዜጋ ፡ የመንግሥቱ ተመረጥኩኘ ፡ እንድኖር ፡ በእርስቱ ፀጋ ፡ ሰጠኝ ፡ የዘለላእም ፡ ደህንነት ታማኝ ፡ ጌታ ፡ ለተደገፉበት ምሥጋናዬ ፡ ይኼው ፡ በየእለቱ ላገልግለው ፡ በደስታ ፡ በቤቱ አዝ፦ ከምንጩ ፡ ስለቀዳሁ ፡ ስለጠጣሁ ፡ ስለረካች ፡ ነፍሴ ምህረት ፡ ስላገኘሁ ፡ አቀርባለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ በደሙ ፡ ስለዋጀኝ ፡ ስላዳነኝ ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ ለኪዳኑ ፡ ስላሰበኝ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጌታዬን ፡ ስባርክ ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ መድህኔ ስላዳነኝ ፡ ከሞት ፡ ከኩነኔ ሥሙ ፡ ይክበር ፡ የጸዮኑ ፡ አለት ተቆረጠ ፡ የኀጢአት ፡ ሰንሰለት አምልኮዬ ፡ ለመድሃኒዓለም ታላቅ ፡ ስሙ ፡ ይመስገን ፡ ዘለዓለም ለሚገዛው ፡ ሠማይን ፡ ምድርን አውጃለሁ ፡ ዘምራለሁ ፡ ክብሩን ለታደገኝ ፡ ለታማኝ ፡ ወዳጄ ዘምራለሁ ፡ በደስታ ፡ ፈቅጄ አወራለሁ ፡ ፍቅሩን ፡ ተዐምራቱን እርሱ ፡ ብቻ ፡ መድሃኒት ፡ መሆኑን አይገርምም ፡ ወይ ፡ በአምላክ ፡ መታሰቤ ላገለግል ፡ ለአመልከው ፡ ቀርቤ የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ አገልጋይ ፡ በቤቱ ሎሌ ፡ አደረገኝ ፡ ጌታ ፡ በችሎቱ ኢየሱስ ፡ ይክበር ፡ ይድመቅ ፡ በሕይወቴ እርሱ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ስሬ ፡ መሰረቴ ጠጥቻለሁ ፡ የዘለዓለም ፡ ውሃ ለመለመ ፡ የነፍሴ ፡ በረሃ አዝ፦ ከምንጩ ፡ ስለቀዳሁ ፡ ስለጠጣሁ ፡ ስለረካች ፡ ነፍሴ ምህረት ፡ ስላገኘሁ ፡ አቀርባለሁ ፡ ክብርና ፡ ውዳሴ በደሙ ፡ ስለዋጀኝ ፡ ስላዳነኝ ፡ የዘለዓለም ፡ አምላክ ለኪዳኑ ፡ ስላሰበኝ ፡ ደስ ፡ ይለኛል ፡ ጌታዬን ፡ ስባርክ ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ መድህኔ ስላዳነኝ ፡ ከሞት ፡ ከኩነኔ ሥሙ ፡ ይክበር ፡ የጸዮኑ ፡ አለት ተቆረጠ ፡ የኀጢአት ፡ ሰንሰለት