Loading
Singer
ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ ልጁ ፡ አደረገኝ ፡ መንፈሱን ፡ ሰጥቶ ፡ ጌታ ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ አገልጋይ ፡ አደረገኝ ፡ በዘይት ፡ ቀብቶ ፡ ጌታ የቅባቱ ፡ ውፍረት ፡ ቀንበሬን ፡ ሰበረው (አሃሃ) የተጫነኝንም ፡ ሸክብ ፡ አወረደው (ኦሆሆ) እስራቴን ፡ ሁሉ ፡ የፈቱ ፡ እጆቹ የምለው ፡ የለኝም ፡ በእውነት ፡ ይባረኩ (፪x) የጐልያድን ፡ ቁመት ፡ የልብሱን ፡ ክብደት (አሃሃ) አትኜ ፡ አይደለሁም ፡ የእርሱን ፡ የጦር ፡ ስልት (ኦሆሆ) ምንም ፡ አይደንቀኝም ፡ ጦሩና ፡ ጡሩሩ ወድቆ ፡ ይከሰከሳል ፡ በፊት ፡ በግንባሩ (፪x) በእኔ ፡ ተማምኗል ፡ አስጥለዋለዉ ስሜንም ፡ አውቋል ፡ ጋርደዋለሁ አለና ፡ ጌታ ፡ በበቀል ፡ ወጥቶ ጠላቴን ፡ ጣለው ፡ እራሱን ፡ መቶ የረሳኸኝ ፡ መስሎት ፡ ጭፍራውን ፡ ሰብስቦ (አሃሃ) ውድቀቴን ፡ እንዲያዩ ፡ ወዳጆቹን ፡ ጠርቶ (ኦሆሆ) ጠአቱን ፡ ቀስሮ ፡ ጉድ ፡ እዩ ፡ ሲላቸው እኔን ፡ አአሰብክና ፡ ሃፍረት ፡ አለበስከው ፡ እህ (፪x) ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ ልጁ ፡ አደረገኝ ፡ መንፈሱን ፡ ሰጥቶ ፡ ጌታ ከምድረ ፡ በዳ ፡ ከሩቁ ፡ ጠርቶ አገልጋይ ፡ አደረገኝ ፡ በዘይት ፡ ቀብቶ ፡ ጌታ ፈርጠም ፡ ወፈር ፡ ያለ ፡ እልያብ ፡ እያለ (አሃሃ) በሰው ፡ የተናቀን ፡ ዳዊት ፡ ይቀብ ፡ ያለ (ኦሆሆ) መረሳቴን ፡ ሽሮ ፡ በኢየሱስ/በልጁ ፡ ያሰበኝ ምትክ ፡ የማይኖረው ፡ ለኔስ ፡ አምላክ ፡ አለኝ (፪x) በእኔ ፡ ተማምኗል ፡ አስጥለዋለዉ ስሜንም ፡ አውቋል ፡ ጋርደዋለሁ አለና ፡ ጌታ ፡ በበቀል ፡ ወጥቶ ጠላቴን ፡ ጣለው ፡ እራሱን ፡ መቶ (፪x)