Loading
ከማይመቹ ፡ ሁኔታዎቼ ካልተመለሱ ፡ ጥያቄዎቼ አንተን ፡ መጠጋት ፡ ተማርኩ ፡ ትዕግስትን ያልክልኝ ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፡ ማለትን (፪x) እምነቴን ፡ ሊጨምር ፡ ሊያጠነክረኝ በእርሱ ፡ መጓደዴን ፡ ከፍ ፡ ሊያደርግልኝ ይበልጡን ፡ እንዳውቀው ፡ እርሱ ፡ ማን ፡ እንደሆነ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ነገር ፡ በህይወቴ ፡ ሆነ (፪x) ለእራሴ ፡ ከማውቀው ፡ በላይ እንደምታውቅልኝ ፡ አውቄያለሁ (፪x) ፈጥነህ ፡ ብትመጣ ፡ ብትገኝ ፡ በቤቴ መቼ ፡ ያልፍ ፡ ነበር ፡ ይህ ፡ ሁሉ ፡ በህይወቴ እንዲህ ፡ ያለውን ፡ ስንፍና ፡ ከአፌ ፡ አላወጣም ሟቹን ፡ ለማስነሳት ፡ እጆችህን ፡ አያጥሩም ድንጋዩን ፡ አንከባለህ ፡ ግንዛቱን ፡ ፈተህ ዳግም ፡ ማመላለስ ፡ ፍቃድህ ፡ ከሆነ ሰው ፡ ሁሉ ፡ አልቅሶ ፡ ሲያበቃ ፡ ከጀመርክ ይሁንልኝ ፡ እላለሁ ፡ ሁሉ ፡ እንደፈቃድህ አይሆንም ፡ ስል ፡ ሆነ አይነጋም ፡ ስልህ ፡ ነጋ አልዘልቅም ፡ ስል ፡ ዘለቅኩ በብዙ ፡ ጀገንኩኝ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ (፪x) የትላንት ፡ ምሽቴ ፡ ምስጋናን : ወለደ የዘገየው ፡ መልሴ ፡ በውበት ፡ ተገለጠ የሌሊት ፡ ለቅሶዬ ፡ ሳቅን ፡ አመጣልኝ ባንተ ፡ ጊዜ ፡ ሲሆን ፡ ነገሬ ፡ አጌጠልኝ አይሆንም ፡ ስል ፡ ሆነ አይነጋም ፡ ስልህ ፡ ነጋ አልዘልቅም ፡ ስል ፡ ዘለቅኩ በብዙ ፡ ጀገንኩኝ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ (፪x) በብዙ ፡ በረታሁ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ በብዙ ፡ ጀገንኩኝ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ በብዙ ፡ በረታሁ ፡ በእርሱ ፡ ስለተያዝኩ ከማይመቹ ፡ ሁኔታዎቼ ካልተመለሱ ፡ ጥያቄዎቼ አንተን ፡ መጠጋት ፡ ተማርኩ ፡ ትዕግስትን ያልክልኝ ፡ ብቻ ፡ ይሁን ፡ ማለትን
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.