Loading
Singer
ያለእርሱ ፡ ፈቃድ ፡ የበላ ፡ ተድላን ፡ የቀመሰ ፡ ማነው እስትንፋስ ፡ ያለው ፡ በሙሉ ፡ ሲመካ ፡ ሚያምረው ፡ በእርሱ ፡ ነው ለሃጥን ፡ ለጻድቁ ፡ ሰው ፡ ፀሐይን ፡ እኩል ፡ ያወጣል በግሌ ፡ ተገርሜርያለሁ ፡ ጌታ ፡ ከአይምሮዬ ፡ ያልፋል አዝ፦ ከማስበውና ፡ ከምገምተው በላይ ፡ ያደረገው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) የለመንኩትን ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ ጨምሮ ፡ ሌላም ፡ ሰጥቶኛል ያልጠበኩትን ፡ በረከት ፡ ፀጋውን ፡ ደርቦልኛል ከእጆቹ ፡ የተቀበልኩት ፡ ስጦታው ፡ እንዴት ፡ መልካም ፡ ነው ቅሬታ ፡ የለም ፡ በልቤ ፡ ያረገው ፡ ሁሉ ፡ መልካም ፡ ነው አዝ፦ ከማስበውና ፡ ከምገምተው (በላይ) በላይ ፡ ያደረገው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) የምህረት ፡ ደጁ ፡ አልተዘጋም አምላኬ ፡ በዚህ ፡ አይታማም እርሱ ፡ እኮ ፡ ባለፀጋ ፡ ነው ለሚፈልጉት ፡ ቅርብ ፡ ነው (፪x) አዝ፦ ከማስበውና ፡ ከምገምተው (በላይ) በላይ ፡ ያደረገው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) ያለእርሱ ፡ ፈቃድ ፡ የበላ ፡ ተድላን ፡ የቀመሰ ፡ ማነው እስትንፋስ ፡ ያለው ፡ በሙሉ ፡ ሲመካ ፡ ሚያምረው ፡ በእርሱ ፡ ነው ለሃጥን ፡ ለጻድቁ ፡ ሰው ፡ ፀሐይን ፡ እኩል ፡ ያወጣል በግሌ ፡ ተገርሜርያለሁ ፡ ጌታ ፡ ከአይምሮዬ ፡ ያልፋል አዝ፦ ከማስበውና ፡ ከምገምተው (በላይ) በላይ ፡ ያደረገው ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)