Loading
Singer
አዝ:- ከለለኝ (፮x) ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነቱ ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነት ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ (፪x) ጠላቴ ፡ ሊያጠፋኝ ፡ ወጥመዱን ፡ ዘርግቶ (አሃ ፡ አሃ ፡ ወጥመዱን ፡ ዘርግቶ) ከግራና ፡ ከቀኝ ፡ የሚረዳኝ ፡ ጠፍቶ (አሃ ፡ አሃ ፡ የሚረዳኝ ፡ ጠፍቶ) ወደ ፡ ተራሮች ፡ ላይ ፡ ዓይኖቼን ፡ ባነሳ (አሃ ፡ አሃ ፡ ዓይኖቼን ፡ ባነሳ) ረዳት ፡ ከወዴት ፡ ይምጣ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲረሳኝ (አሃ ፡ አሃ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ሲረሳኝ) የማይረሳ ፡ አምላክ ፡ ድንገት ፡ ያስባል ምስክሩ ፡ ነኝ ፡ እኔን ፡ ረድቶኛል ሰማይን ፡ ቀዶ ፡ ወርዶ ፡ አሳረፈኝ አባት ፡ አለኝ ፡ ልበል ፡ እንዴት ፡ ደስ ፡ አይለኝ (፪x) አዝ:- ከለለኝ (፮x) ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነቱ ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነት ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ ቀድሞኝ ፡ እየወጣ ፡ ከፊት ፡ ፊት ፡ ሲመራኝ (አሃ ፡ አሃ ፡ ከፊት ፡ ፊት ፡ ሲመራኝ) አልረሳም ፡ ካችሃምና ፡ እንዴት ፡ እንደረዳኝ (አሃ ፡ አሃ ፡ እንዴት ፡ እንደረዳኝ) እንደ ፡ ዐይኖቹ ፡ ብሌን ፡ ተተንቅቆልኛል (አሃ ፡ አሃ ፡ ተጠንቅቆልኛል) አፌን ፡ ሞልቼ ፡ ልበል ፡ እግዚአብሔር ፡ ያድናል (አሃ ፡ አሃ ፡ አምላኬ ፡ ያድናል) ውዴን ፡ ተደግፌ ፡ ወጣሁ ፡ ከበረሃ ዙሪያዬን ፡ አጠረው ፡ ደስታና ፡ ፍሰሃ የማምለጫ ፡ አለት ፡ ጽኑ ፡ ግንብ ፡ ሆኖኛል ጥበቃውን ፡ ሳስብ ፡ ዘምር ፡ ያሰኘኛል (፪x) አዝ:- ከለለኝ (፮x) ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነቱ ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ ከለለኝ ፡ በምህረቱ ፡ ከለለኝ ፡ በቸርነት ከለለኝ ፡ በደግነቱ ፡ ከለለኝ ፡ በበጐነቱ