Loading
Singer
አዝ:- ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x)) ከእኔ ፡ ችግር ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x)) ብዙ ፡ ጥያቄ ፡ እንቆቅልሽ ፡ እያለኝ ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ ሁሌ ፡ ደስተኛ ፡ ነኝ ለእኔ ፡ የተከፈለው ፡ ትልቅ ፡ የደም ፡ ዋጋ አይመጣጠንም ፡ ከሁኔታዬ ፡ ጋር አዝ:- እንቆቅልሼ ፡ እያለ ችግር ፡ መከራ ፡ እያለ ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ ድል ፡ አለ ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ መልስ ፡ አለ (፪x) ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x)) ከእኔ ፡ ችግር ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x)) በእንግድነት ፡ አገር ፡ ለጊዜው ፡ ምኖረው በምታልፈው ፡ ዓለም ፡ ትቼው ፡ ለምሄደው ቢሞላ ፡ ባይሞላ ፡ እኔ ፡ ምን ፡ ቸገረኝ ስሄድ ፡ ምገባበት ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ አለኝ አዝ:- እንቆቅልሼ ፡ እያለ ችግር ፡ መከራ ፡ እያለ ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ ድል ፡ አለ ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ መልስ ፡ አለ (፪x) ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x)) ከእኔ ፡ ችግር ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x)) እንዳላጉረመርም ፡ አፌን ፡ በምሥጋና ሃዘንተኛ ፡ እንዳልመስል ፡ ፊቴ ፡ እያበራ ኢሄ ፡ እንዴት ፡ ሆነ ፡ ለምትጠይቁኝ ሁሉን ፡ የሚያስረሳ ፡ አባት ፡ ስላለኝ አዝ:- እንቆቅልሼ ፡ እያለ ችግር ፡ መከራ ፡ እያለ ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ ድል ፡ አለ ግን ፡ እዘምራለሁ ፡ መልስ ፡ አለ (፪x) ከሁኔታ ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x)) ከእኔ ፡ ችግር ፡ በላይ ፡ ጌታ ፡ የበላይ (፪x) (ጌታ ፡ የበላይ (፪x))